የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ናይሮቢ ተገናኙ

ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሶማሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ተቀብለዋል።

ኬንያ እና ሶማሊያ ወደ አገራቸው የሚደረጉ በረራዎችን አግደው ነበር።

የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሁሴን መሐመድ ሮብሌ በናይሮቢ ይፋዊ ጉብንታ እያደረጉ መሆኑን የኬንያ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አስታውቋል።

የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታም በሀገራቸው ጉብኝት ላይ የሚገኙትን የሶማሊያውን ጠቅላይ ሚኒስትር ሁሴን መሐመድ ሮብሌን ተቀብለው ማነጋገራቸውን ጽ/ቤታቸው ገልጿል። ጽ/ቤቱ እንዳስታወቀው መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ይወያያሉ።

ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን አቋርጠው የነበሩት ኬንያ እና ሶማሊያ ለመልካም ጉርብትና ሲባል ግንኙነታቸው ዳግም እንዲጀመር ማድረጋቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።

“መልካም ጉርብትና ይሻላል” በሚል ግንኙነት እንዲጀመር ያደረገችው ሞቃዲሾ እንደነበረች ይታወሳል፡፡

ሶማሊያ፤ የኬንያ መንግስት በተደጋጋሚ ለሚፈፅማቸው የፖለቲካ ጥሰቶች እና ግልፅ ጣልቃ ገብነት ምላሽ ለመስጠት በሚል ከጎረቤቷ ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን ገልጻ ነበር።

ሶማሊያ በኬንያ “ደረሰብኝ“ ላለችው ግልጽ ጣልቃ ገብነት ምክንያት አምባሳደሯን ከናይሮቢ ወደ ሞቃዲሾ ጠርታም ነበር።

በተጨማሪም ሶማሊያ፤ ከናይሮቢ ወደ ሞቃዲሾ የሚደረጉ ማናቸውንም የአውሮፕላን በረራዎች አግዳ የነበረ ሲሆን የሁለቱ ሀገራት የውጭ ግንኙነትም ወደ ከፋ ደረጃ ተሸጋግሮ እንደነበር ተንታኞች ሲገልጹ ቆይተዋል።

ሶማሊያ እና ኬንያ በህንድ ውቂያኖስ ዳርቻ ይገባኛል በሚል ግጭት ውስጥ ገብተው የነበረ ሲሆን ሄግ የሚገኘው የግልግል ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲሰጥ ሶማሊያ ጥያቄ አቅርባ የነበረ ቢሆንም ኬንያ ክርክሩን ማቋረጧ ይታወሳል።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe