ተጠባባቂው የሀያላኑ ሀገራት መሪዎች ውይይት ዛሬ ይደረጋል።
የቻይናዋ ሼንዠን ከተማ ይህንን ታሪካዊ ውይይት የምታስተናግደዋ ከተማ ነች።
የዓለም ሦስቱ ሀያላን ሀገራት መሪዎች በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ የሦስትዮሽ ስብሰባ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
የአሜሪካው ዶናልድ ትራምፕ፣ የሩሲያው ቭላድሚር ፑቲን፣ የቻይናው ዢ ጂንፒንግ ዛሬ ሐሙስ ተገናኝተዋል።
ትራምፕ ታሪካዊ ከሆነው ከዚህ የሦስትዮሽ ውይይት በፊት ከፑቲን እና ከዢ ጋር በተናጠል ተገናኝተው ተወያይተዋል።
በሼንዠን በሚካሄደው የኤፔክ (APEC) ጉባኤ ላይ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፑቲን እና ከዢ ጋር የአንድ ለአንድ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ ከሁለቱም መሪዎች ጋር ታይቶ የማይታወቅ የጋራ ስብሰባም ያካሂዳሉ።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቻይናዋ ሼንዠን ከተማ እየተካሄደ ካለው አህጉራዊ ጉባኤ ጎን ለጎን እና ዛሬ በሦስቱ መሪዎች መካከል ከሚደረገው ወሳኝ ውይይት አስቀድሞ ከዢ ጂንፒንግ እና ከቭላድሚር ፑቲን ጋር በተናጠል ተገናኝተዋል።
ዢ ቀደም ሲል የእስያ-ፓስፊክ የኢኮኖሚ ትብብር መድረክ (APEC) አባል የሆኑ 20 ሌሎች የፓስፊክ ቀጠና ኢኮኖሚ መሪዎችን ተቀብለዋል።
የትራምፕ እና የዢ ውይይት ከአንድ ሰዓት ገደማ በኋላ መጠናቀቁን የቻይና መንግሥታዊ ቴሌቪዥን (CCTV) ዘግቧል።
በትራምፕ እና በፑቲን ውይይት ላይ የተገኙት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ረዳት ዩሪ ኡሻኮቭ፣ የስብሰባው ዋና አጀንዳ ዩክሬን እንደነበረች እና ከውይይቱ በኋላ የፑቲን ስሜት እጅግ በጣም ጥሩ እንደነበር ገልጸዋል።
ትራምፕ ዛሬ ለዢ አድናቆታቸውን የገለጹ ሲሆን ከቻይናው መሪ ጋር የገነቡትን ወዳጅነትም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ እሳቸው እና ዢ ባለፉት ዓመታት “ድንቅ የግል ግንኙነት መመሥረታቸውን እና የሁለቱንም ሀገራት ሕዝቦች በሚገባ ማገልገላቸውን ገልጸዋል።
ከኤፔክ አህጉራዊ ጉባኤ ጎን ለጎን በተደረገው ስብሰባ መጀመሪያ ላይ ንግግር ያደረጉት ትራምፕ፣ ሁለቱ ወገኖች የደረሱባቸውን ስምምነቶች አሞካሽተዋል።
አሜሪካም ሆነች ቻይና በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ የኃይል አቅርቦት እንዲቀጥል ፍላጎት አላቸው ሲሉ ትራምፕ ከዢ ጋር በተገናኙበት ወቅት ተናግረዋል።
ትራምፕ ከዢ ጋር የተገናኙት ከፑቲን ጋር ካደረጉት ውይይት በኋላ ወዲያውኑ ነው።
ትራምፕ ከዢ ፊት ለፊት በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው አሜሪካም ሆነች ቻይና በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ በኩል የኃይል አቅርቦት እንዲቀጥል የማረጋገጥ ፍላጎት አላቸው ብለዋል።
ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ልትታጠቅ አትችልም፤ በዚህ ጉዳይ ሁለታችንም በጣም ጠንካራ አቋም አለን ሲሉ ተናግረዋል። አክለውም “በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ያለውን ጦርነት በተመለከተ ሁለታችንም ለመርዳት እየፈለግን ነው” ብለዋል።
ከዢ እና ከፑቲን ጋር ስለሚያደርጉት የሦስትዮሽ ስብሰባም ምናልባት ስኬታማ ስብሰባ የሚኖረን ይመስለኛል ብለዋል።//
የዓለም ሦስቱ ሀያላን ሀገራት መሪዎች በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የሦስትዮሽ ስብሰባ ዛሬያካሂዳሉ

