‹‹የዓመቱ ሰዎች››

ደራርቱ ቱሉ
በአፍሪካ የአትሌቲክስ ታሪክ ቀዳሚዋ ሴት የሆነችው ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ ወደስፖርቱ አመራርነት ገብታም ስኬታማ እየሆነች ነው፡፡ ሻለቃ ሀይሌ ገ/ስላሴ ራሱን ከሃላፊነት ካነሳ በኋላ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በፕሬዝዳንትነት የምትመራው ደራርቱ ባለፈው ሰሞን ደግሞ የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና በሙሉ ድምፅ ተመርጣለች።
ከዚህ በተጨማሪም ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ በአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን /CAA/ ውስጥ ሪጅኑን በመወከል የቦርድ አባል ሆናም ተመርጣለች።
የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ኮንግረስ ስብሰባ በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ ነበር ደራርቱ የተመረጠችው፡፡
ስኬታማዋ አትለት ደራርቱ ቱሉ ከኦሎምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈፃሚነት ራሷን ለማግለል ያሳለፈችውን ውሳኔ ያሳወቀችውም በተጠናቀቀው አመት ነበር፡፡ የኮሚቴው አመራሮች አግልለውኛል በሚል ነው ራሷን ከቦርዱ ያስወጣችው፡፡ ይሁን እንጅ ኋላ ላይ ውሳኔዋን ማጠፏን አስታውቃለች፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በፕሬዝዳንትነት የምትመራው ደራርቱ በውሳኔ አሰጣጥ ረገድ የምትመለከታቸውን ሕጸጾች ከዚህ በኋላ የማይታረሙ ከሆነ ከኦሎምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈፃሚነት ራሷን እንደምታገል ማስጠንቀቋን ገልጻለች።
በደብረ ብርሀን ከተማ በተደረው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከሥራ አስፈፃሚነት ለመልቀቅ መወሰኗን የተናገረችው ደራርቱ በጠቅላላ ጉባኤው በርካታ ሰዎች ውሳኔዋን እንድታጥፍ ግፊት ማሳደራቸውን ተከትሎ ነው ውሳኔዋን የቀየረችው፡፡
«ከዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ እና እርሳቸው ከሚመሩት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በተፈጠረ መቃቃር ምክንያት» ከኦሎምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈፃሚነት ደራርቱ ራሷን ለማግለል አስገድዷት ነበር።
በታላቁ የአፍሪካውያን ሩጫ በዲሲ አዘጋጅ የሆነው ኮሚቴ ደራርቱ ቱሉን የሸለመውም በተጠናቀቀው አመት ነው፡፡
አትሌት ደራርቱ ቱሉ ከኦሎምፒክ ሜዳሊያዎችን በማሸነፍ ከአፍሪካ ቀደምት ተብላ የተሸለመች ሲሆን አትሌት ደራርቱ በተወዳደረችባቸው ሩጫዎች ሰላሳ አምስት ወርቅ አስራ ሁለት ብርና አስራ አምስት የነሃስ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች። ይህ ደግሞ አትሌት ደራርቱን ከ አፍሪካ ብቸኛና የመጀመሪያዋ የሜዷሊያዎች አሸናፊ አድርጓታል። ኮሚቴው ለዚህ ላበረከተችው አስታውጽኦ እውቅናና ሽልማት ሰጥቷታል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe