“የግድቡን ሁለተኛ ዙር ሙሌት ለማከናወን ሁሉም ዝግጅት ተጠናቋል” አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር)

“ዓባይ ራሱን የሚጠብቅበት ደረጃ ላይ ደርሷል፤ ዓባይን የሚነካ ይበላል” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

“ኢትዮጵያ፤ የሕዳሴ ግድብን ለማጠናቀቅ የገንዘብ ችግር የለባትም” ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ በመገንባት ላይ የምትገኘውን የሕዳሴ ግድብ ለማጠናቀቅ “የገንዘብ ችግር እንደሌለባት” የግድቡ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

የጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) ከአል ዐይን አማርኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድጋፍ አግኝታ ግድቡን እንዳትገነባ ቢደረግም፣ ፕሮጀክቱን ለመጨረስ የኢትዮጵያ ሕዝብ እጁ እንደማያጥር አንስተዋል፡፡

አል ዐይን አማርኛ የሕዳሴ ግድብን ለማጠናቀቅና በገንዘብ ለመደገፍ አሁን ላይ ችግር አለ ወይ በሚል የተጠየቁት አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር)፣ “አሁን ላይ ግድቡን ለማጠናቀቅ ምንም አይነት የገንዘብ ችግር የለም“ ብለዋል፡፡

የግድቡን ሁለተኛ ዙር ሙሌት ለማከናወን “ሁሉም ዝግጅት ተጠናቋል“ ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የሚጠበቀው ክረምቱ ብቻ መሆኑን አንስተዋል፡፡ “ግድቡ መድረስ ያለበት የግንባታ መጠን 595 ሜትር እንዳልደረሰና በዚህም ምክንያት ሁለተኛውን ዙር ሙሌት ማካሄድ እንደማይቻል” ከግብፅ እና ሱዳን እየተነሳ ያለው መረጃ ውሸት መሆኑን አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

የውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትሩ ዶ/ርስለሺ በቀለም እንዲሁ ግንባታው ለሁለተኛ ዙር የታቀደውን የውሃ ሙሌት ለማከናወን “እንዳልደረሰ” በመግለጽ የሚሰራጩ መረጃዎች ሀሰት መሆናቸውን ገልጸው ፣ የግድቡ “ሁለተኛ ሙሌት በተያዘው ክረምት የግድ እንደሚከናወን” ዛሬ ተናግረዋል፡፡

ግድቡን በተመለከተ ግብፅ እና ሱዳን ለተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም/ቤት አቤቱታ ማቅረባቸው፣ እንዲሁም የአረብ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ መቀመጥ ኢትዮጵያን ጫና ውስጥ እንደማይከታትም አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ፣ በየትኛውም በኩል ለሚመጣ ዓለም አቀፍ ጫና እንደማትንበረከክም የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ግድቡ የኢትዮጵያውያን የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ከቀጣ ምርጫም ሆነ ከሌሎች ሀገራዊ ሁነቶች እንደሚበልጥ ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር አረጋዊ አክለውም ዓባይ ራሱን የሚጠብቅበት ደረጃ ላይ ደርሷል፤ ዓባይን የሚነካ ይበላል ሲሉ የግድቡ ሁለተኛ ሙሌት ከደህንነት ጋር የተያያዘ ትርጉም እንዳለውም ገልጸዋል፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe