የፀጉርሽን ውበት ለመጠበቅ የሚረዱ ዘዴዎች

በርካታ ሴቶች የፀጉራቸውን ሁኔታ በመስታወት እያዩ በየቀኑ ብዙ ስዓት ያሳልፋሉ፡፡ የተቻለውን ያህል ጥረት በማድረግም ውበቱን ለመጠበቅ ይጥራሉ፡፡ ከእነዚህ ሰዎች ውስጥ አንቺ አንዷ ልትሆኚ ትችያለሽ፡፡ የፀጉርሽ አቆራርጥ፣አበጣጠርና አሰራር የአንቺነትሽ መገለጫ መስታወትሽ ነው፡፡ ፀጉርሽ ስለአንቺ ብዙ ብዙ ይናገራል፡፡ ፀጉሯን አስውባና አሳምራ የምትሄድን ሴት ስትመለከቺ ምን እንደሚሰማሽ አስተውለሽ ታውቂያለሽ? ጠንቃቃና ስለራሷ የምትጨነቅ መሆኗን ለራስሽ ትነግሪያለሽ፡፡ ታዲያ ፀጉር ስለባለቤቱ እንደሚናገር አልተረዳሽም? ለማንም ያልተነፈሽውን ውስጥሽን ፀጉርሽ የሚያሳብቅብሽ ከሆነ ልትንከባከቢው ግድ ይልሻል፡፡

የፀጉርሽን ውበት ለመጠበቅ የሚረዱ ዘዴዎች

  1. ፀጉርሽን ከመታጠብሽ በፊት ቆዳሽን ፈሳሽ ቅባት ተቀቢ፡፡ በእጅሽም ቆዳሽን እሺው፡፡ ይህ ቆዳ እንዲለሰልስና እንዲታደስ ያደርገዋል፡፡ ከመታጠብሽ በፊትም ለግማሽ ስዓት ወይም ለጥቂት ደቂቃ አቆይው፡፡
  2. የፀጉርን ውበት ለመጠበቅ ዋንኛው ዘዴ በየጊዜው መታጠብ ነው፡፡ ፀጉርን እንደ ሻምፖና ሳሙና ባሉ የፀጉር ማፅጃዎች መታጠብ ተገቢ ነው፡፡ የላቭሊ የውበት ስራ ማስልጠኛና የውበት ሳሎን የፀጉር ባለሙያ የሆነው አቶ ጎልያድ ሚካኤል ፀጉርን በሻምፖ ብቻ መታጠብ የሚመከር እንደሆነ ነው የሚናገረው፡፡ ፀጉርሽን በየስንት ጊዜው መታጠብ እንዳለብሽ አስቀድመሽ ልታወቂ ይገባል፡፡ ፀጉርሽን በታጠብሽ በማግስቱ ቅባታማ ከሆነ ፀጉርሽ ወዛም ስለሆነ በሳምንት ሦስት ጊዜ ልትታጠቢ ይገባሻል፡፡ ምክንያቱም የፀጉርሽ ቅባት ከቆሻሻና እንደፎሮፎር ካሉ ብናኞች ጋር በመሰባሰብ የቆዳሽን ቀዳዳ ይደፍናል፡፡ ደረቅ ፀጉር ካለሽ በሳምንት አንድ ጊዜ ብቻ መታጠቡ በቂ ነው፡፡ ፀጉርሽ መካከለኛ ከሆነ በሳምንት ሁለቴ ታጠቢ፡፡ በምትታጢበት ጊዜም የሞቱ ህዋሳትን ከቆዳሽ ለማስወገድ ይረዳሽ ዘንድ ቆዳሽን በደንብ ፈትጊ፡፡ ሻምፖውንም ምልጭ አድርጎ መለቅለቁን አትርሺ፡፡
  3. ሻምፖውን በሚገባ ከታጠብሽ በኋላ ፀጉርሽን ለማፍታታት ኮንዲሽነር ተጠቀሚ፡፡ ኮንዲሽነር ለማንኛውም አይነት ፀጉር ውበትን የሚያጎናጽፍ ሲሆን በተለይ በተፈጥሮ ፀጉርሽ ደረቅ ከሆነ አንፀባራቂ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ፀጉርሽ ሉጫም ሆነ ከርዳዳ፣ረጅምም ሆነ አጭር፣ወፍራምም ሆነ ስስ ለሁሉም ዓይነት ፀጉር ኮንዲሽነር አስፈላጊ ነው፡፡ የፀጉርሽን ልስላሴና ወዝ ጠብቀሽ ለማቆየት ኮንዲሽነርን በሳምንት ሶስት ጊዜ እንድትጠቀሚ ትመከሪያለሽ፡፡ በተለይ ፀጉርሽ ረጅም ከሆነ የተፈጥሮ የፀጉር ቅባትሽ ጫፍ ድረስ ስለማይደርስ ፀጉርሽ መንታ ያወጣል፡፡ ይህን ለመከላከልም ኮንዲሽነር ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡ ኮንዲሽነርን ተቀብተሸ ከ10-15 ደቂቃ ፀጉርሽን እንዲፍታታ ያደርገዋል፡፡ ሁለት አይነት ኮንዲሽነር አለ፡፡ አንዴ ፀጉርሽ ላይ ከተቀባሽው መለቅለቅ የማያስፈልግሽ (leave-in) ኮንዲሽነር ሲሆን ሌላኛው ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ከፀጉርሽ የሚለቀለቀው ነው፡፡
  4. ፀጉርሽን በኮንዲሽነር መሀሉን እየከፈልሽ ቅባት ቀቢው፡፡ ቅባት የፀጉር መብቂያ እንዲታደስና ፀጉርም ጤነኛና አንፀባራቂ እንዲሆን ይረዳል፡፡ የተለያዩ የቅባት አይነቶች ያሉ ሲሆን የሚስማማሽን መምረጥ ይኖርብሻል፡፡ ቅባቱን ከተቀባሽ በኋላ በእጅሽ ቆዳሽን ማሽቱ ለጠንካራና ጤነኛ ፀጉር ወሳኝ ነው፡፡ ይህ ወደጭንቅላት የሚፈሰው ደም የተስተካከለ እንዲሆን ይረዳል፡፡ በደንብ ማበጠርንም አትርሺ፡፡
  5. የመጨረሻ ደረጃ የሚሆነውም ፀጉርሽን ከፊትሽ ጋር በሚስማማ መልኩ መሰራት ነው፡፡ በቢጎድን በመጠቅለል፣በካውያ ወይም በፔይስትራ በመስራት ፀጉርን ስታይል ማስያዝ ይቻላል፡፡ እንደምርጫሽ ልታደርጊው ትችያለሽ፡፡ ጤነኛና ውብ ፀጉር ነዋ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe