“የ2026 የዓለም ዋንጫ እና አዳዲስ ክስተቶች”

የ2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ ከሰኔ 4 እስከ ሐምሌ 12/ 2018 ዓ.ም. የሚካሄድ ሲኾን፣ በሦስት አገራት (ካናዳ፣ ሜክሲኮ እና አሜሪካ) በጋራ በመሰናዳት የመጀመሪያው ነው።
የተሳታፊ አገራት ቁጥር ወደ 48 በማደጉ በታሪክ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ይህ ውድድር አጠቃላይ የጨዋታዎቹን ቁጥር ወደ 104 ከፍ አድርጎታል።
ዋና ዋና የውድድሩ እውነታዎች
አስተናጋጅ ከተሞች
ጨዋታዎቹ በ16 ከተሞች ውስጥ ይካሄዳሉ፤ 11 ከተሞች በአሜሪካ (አትላንታ፣ ቦስተን፣ ዳላስ፣ ሂውስተን፣ ካንሳስ ሲቲ፣ ሎስ አንጀለስ፣ ማያሚ፣ ኒው ዮርክ/ኒው ጀርሲ፣ ፊላዴልፊያ፣ ሳን ፍራንሲስኮ እና ሲያትል)፣ 3 ከተሞች በሜክሲኮ (ጓዳላሃራ፣ ሜክሲኮ ሲቲ እና ሞንቴሬይ) ሲካሄዱ 2 ከተሞች ደግሞ በካናዳ (ቶሮንቶ እና ቫንኩቨር ከተሞች ) ይህን የአለም ዋንጫ ያስተናግዳሉ።
የመክፈቻ እና የፍፃሜ ጨዋታዎች
ውድድሩ ሰኔ 4/2018 ዓ/ም በሜክሲኮ ሲቲ በሚገኘው ታዋቂው ኤስታዲዮ አዝቴካ ስታዲየም ይጀምራል። የፍፃሜው ጨዋታ ደግሞ ሐምሌ 12/ 2018 ዓ/ም በአሜሪካ ኒው ጀርሲ በሚገኘው ሜትላይፍ ስታዲየም ይደረጋል።
የተቀየረው የውድድር ቅርፅ
48ቱ ሀገራት በ12 ምድብ በአራት ተከፍለው የሚጫወቱ ሲሆን፣ የእያንዳንዱ ምድብ መሪዎችና ሁለተኛ ሆነው የሚያጠናቅቁት እንዲሁም ስምንት ምርጥ ሦስተኛ የወጡት ሀገራት ወደ ምርጥ 32 ቡድኖች የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ያልፋሉ።
ማስኮቶች (መለያ ምልክቶች)
እያንዳንዱ አስተናጋጅ ሀገር የራሱ ማስኮት ያለው ሲኾን ሜፕል ዘ ሙዝ (ካናዳ)፣ ዛዩ ዘ ጃጓር (ሜክሲኮ) እና ክለች ዘ ባልድ ኢግል (አሜሪካ) ናቸው።
ክብረወሰን
ሜክሲኮ የወንዶች የፊፋ ዓለም ዋንጫን ከዚህ ቀደም በ1970 እና በ1986 ካስተናገደች በኋላ፣ አሁን ደግሞ ለሦስተኛ ጊዜ በማስተናገድ (ወይም በጋራ በማዘጋጀት) የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች።
አዲስ ተሳታፊዎች
የቡድኖች ቁጥር መጨመሩ አራት አገራት ማለትም ኬፕ ቨርዴ፣ ኩራሳኦ፣ ጆርዳን እና ኡዝቤኪስታን ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ዋንጫ ላይ እንዲሳተፉ ዕድል ፈጥሮላቸዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe