የG7 ሀገራት መሪዎች ላለፉት 3 ቀናት ሲያደረጉ የነበሩትን ስብሰባ ዛሬ አጠናቀዋል። በስብሰባው መጠናቀቅ በኃላም ባለ 70 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል። ከዚህ ቀደም መረጃዎችን እንደተለዋወጥነው ከG7 ስብሰባ አጀንዳዎች መካከል የኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ጉዳይ አንዱ እኛ ዋነኛው ነበር።
የG7 ሀገራት ስብሰባው ማጠቃለይ ስለትግራይ ምን አሉ ?
– ትግራይ ውስጥ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
– በ100 ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ለረሃብ መጋለጥ፣ በክልሉ የቀጠለው ግጭት፣ አጠቃላይ እየተፈጠረ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ አሳስቦናል ብለዋል።
– ጠብ ጫሪነት ተግባራት በፍጥነት እንዲቆሙ ፣ በሁሉም አካባቢዎች የእርዳታ ድርጅቶች ያልተገደበ እንቅስቃሴ እንዲፈቀድላቸውና የኤርትራ ወታደሮች በአፋጣኝ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
– በትግራይ ክልል ተፈጽመዋል ያሏቸውን ፆታዊ ጥቃቶችን ፣ አሰቃቂ ግድያዎችን እና ድርጊቶችን አውግዘዋል።
– የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የፈጸሙ አካላት ለፍትህ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።
– በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የተጀመረውን ምርመራ በደስታ እንደሚቀበሉ ገልጸዋል።
– ሁሉም ወገኖች ለቀውሱ ብቸኛ መፍትሔ የሆነውን ተዓማኒ የፖለቲካ ሒደት እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።
– የኢትዮጵያ መሪዎች ብሔራዊ እርቅ እና መግባባት የሚፈጥር ሰፊ እና አካታች የፖለቲካ ሂደት እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።

