ይልቅ ወሬ ልንገርህ – ስለ ሀገሪቱ ፖለቲካዊ ሁነቶች በአልባሳት አሰያየም ላይ

ከሰሞኑ ምናልባት ትግራይ ሄደው በአንደኛው ልብስ መሸጫ መደብር ውስጥ ‘ደብረጽዮን’ አለ? ሲባል ሲሰሙ ምናልባት የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት እዚህ ሱቅ ውስጥ እንዴት ይኖራሉ? የሚል ስሜት ሊፈጥርብዎት ይችላል ይላል የቢቢሲ የሰሞኑ ዘገባ።
ነገር ግን የሃገር ባህል ልብስ መሆኑን ሲሰሙ ይገረሙ ይሆን? እንዴት ነው ስያሜውን ያገኘውስ የሚል ጥያቄን ይጭርብዎት ይሆናል።
በየአመቱ ከነሐሴ 14 ጀምሮ ለሶስት ቀናት በአማራ ክልል በሰቆጣና በላሊበላ ሻደይ፣ አሸንድየ፤ በትግራይ ክልል አሸንዳ ክብረ በዓል ሴቶችን ማዕከል በማድረግ እየተከበረ ነው።በዚህም ክብረ በዓልም ዋነኛው ትኩረት አልባሳት ሲሆን በየአመቱም አዳዲስ የልብስ ዲዛይኖችም የሚታዩበት ነው።
በዚህ አመትም በትግራይ ክልልና በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ህብረ ቀለም ያሸበረቁ ልብሶች ቀርበዋል።ከዚህም በተጨማሪ የሃገሪቱ ወቅታዊና የፖለቲካ ግለቶች የተንፀባረቁባቸው የአልባሳት ስያሜዎችም ተሰጥተዋቸዋል።
በመቐለ ከተማ የሃገር አልባሳትን በመስፋት ሽርጉድ ሲል ቢቢሲ ያገኘው የማነ ለቢቢሲ እንደገለፀው በዚህ አመት ዋነኛ ተፈላጊው ልብስ ደብረፅዮን የሚል ስም ተሰጥቶታል።ደብረፅዮን የሚባለው ልብስ የትግራይ ክልል ሰንደቅ አላማ በዋነኝነት ይዟል።“ዘንድሮ በጣም ተፈላጊ የሆነው ይሄው ‘ደብረጽዮን’ የሚባለውነው። ብዙዎቹም እየሸመቱት ነው። የትኛው ነው ደብረጽዮን እያሉ ይጠይቁንና ይወስዱታል” ብሏል።
ትግራይ በዚህ አመት ህይወታቸውን ያጡ ጄኔራሎችን በአልባሳት ስምም እየዘከረቻቸው ነው።ከዚህ በተጨማሪ በቀድሞው የመረጃና ደህንነት ኃላፊ ጌታቸው አሰፋ፣ በዚህ አመት ህይወታቸውን ባጡት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የተሰየመው ሰዓረ መኮንን እንዲሁም ሜጀር ጄኔራል ገዛኢ አበራ እና ጌታቸው ረዳ በመሳሰሉት የተሰየሙ አልባሳትም ለገበያ ቀርበዋል።
አንደኛው ደረጃ ልብስም በሜትር 170 ብር እየተሸጠ እንደሆነ ሪፖርተሮቻችን ታዝበዋል።ቀደም ሲል የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ የመጡበት ወቅት ስለ ነበር ‘ኦባማ’ የሚባል ልብስ አንደኛ ሆኖ ሲሸጥ ነበር።ከእሱ በኋላም በቃና የቴሌቪዥን ጣብያ ‘ቃና’ የሚል ልብስ ተወዳጅ ሆኖ ገበያውን ተቆጣጥሮት እንደነበርም ቢቢሲ ያናገራቸው ግለሰቦች ተናግረዋል።
ልጃገረዶቹ ብቻ ሳይሆን በሚዲያዎችም ባህላዊ ልብሳቸውን አሸንዳን እንዲያከብሯት በሚድያ ቅስቀሳ ሲደርግ ተስተውሏል።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe