ዳሸን ባንክ ከግብር በፊት 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ትርፍ አስመዘገበ

የዳሸን ባንክ ባለአክሲዮኖች ባለፈው ሳምት መጨረሻ  ባካሄዱት መደበኛና ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባንኩ ከግብር በፊት 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ እንደገለፁት  ባንኩ ባለፈው ዓመት 10.3 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱንና 7.8 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን ጠቁመው፣ ከታክስ በፊት የባንኩ ዓመታዊ ትርፍም 2.4 ቢሊዮን ብር መሆኑን ገልጸዋል፡፡ባንኩ ከታክስ በፊት ያስመዘገበው የትርፍ መጠን ከቀዳሚው ዓመት ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ ያለው ነው፡፡

ዳሸን ባንክ ከአፍሪካ ቀዳሚ ባንኮች አንዱ ለመሆን ይዞ የተነሳውን ራዕይ ለማሳካት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን የገለጹት አቶ አስፋው፣ በተለይ ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረጉ የባንክ አገልግሎቶች ላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት እያደረገ መሆኑን አክለዋል፡፡

ባንኩ ቁጠባን ለማሳደግ፣ በክፍያ ካርድ የታገዘ ዘመናዊ ግብይትን ለማበረታታትና ዓለም አቀፍ ሐዋላንና ክፍያን ለማሳለጥ የሚረዱ አዳዲስ አገልግቶችን ማስተዋወቁ ተገልጿል፡፡ በሒሳብ ዓመቱ የባንኩ ስኬት ብለው ከጠቀሷቸው መካከል ባንኩ በበጀት ዓመቱ 21.1 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ መቻሉንና የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ መጠን 74.6 ቢሊዮን ብር ማድረሱ ይገኙበታል፡፡

የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል አሁን ካለበት 5.4 ቢሊዮን ብር ወደ 12 ቢሊዮን ብር  ለማሳደግ የቀረበው ሐሳብ ተደግፎ ፀድቋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe