በቪዥን እና ግሎባል ትሬንድስ የዓለም አቀፍ የትንታኔዎች ኢንስቲትዩት ሊቀመንበር ቲቤሪዮ ግራዚያኒ ዶናልድ ትራምፕ ከቭላዲሚር ፑቲን ጋር የሚገናኙበትን ቦታ አላስካ ያደረጉበት ሁለት ምክንያቶችን ጠቅሰዋል።
የአስተዳደራቸውን የአሜሪካን “የዲፕሎማሲ ሚና ማሻሻል”፣ አሜሪካ እና ሩሲያ በክልሉ የሚጋሩት የጋራ ታሪክ እና የሚገኝበት ቦታ፤ የሁለቱን መሪዎች ቅርበት እና በትራምፕ እና በአውሮፓ ኅብረት መካከል ያለውን ርቀት የሚያጎላ በመሆኑ።
ድርድሩ በዩክሬን ላይ ብቻ የሚያተኩር ሳይሆን ሩሲያ በብራሰልስ እና ለንደን የሚታዩ ፍላጎቶች ዙሪያ የተደቀኑባትን “የህልውና ስጋቶች” የሚያቃልል እንዲሁም አሜሪካ አውሮፓ ውስጥ ላሏት ጥቅሞች እውቅና የሚሰጥ “የደህንነት ሥርዓት ማዋቀርን” ሊያካትት ይችላል።
ግራዚያኒ መሪዎቹ “የዓለምን ሥርዓት መልሰው ለማዋቀር እየሠሩ ነው” ብለዋል።
ሆኖም ሁለቱ የዓለም መሪዎች የተለያዩ ግቦች እንዷላቸው ገልጸዋል፡፡ ትራምፕ “በአዲሱ ባለብዙ-ማዕከል ዓለም አቀፍ ሥርዓት ውስጥ የበላይነታቸውን ማስጠበቅ” ሲፈልጉ፤ ፑቲን በበኩላቸው “የደቡባዊውን ዓለም ሀገራት ወደ ውይይት እና ውሳኔ ሰጪነት ሂደት በማምጣት አዲሱን ዓለም አቀፍ ሥርዓት መቅረፅ” ይሻሉ ብለዋል።

