የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 5ኛ ዓመት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የቀረቡ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባላትን ሹመት መርምሮ አፅድቋል፡፡
በዚህ የዛሬው የፖርላማ ውሎ ላይ ለፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባልነት ከቀረቡት ስምንት ተሻሚዎች መሀከል የዲያቆን ዳንኤል ክብረት እጩነት የፖርላማ አባላቱን ሲያጨቃጭው ውሏል፡፡ የቦርድ አባላቱ ተሻሚዎች ማንነት በፖርላማው የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ በሆኑት የተከበሩ አቶ መስፍን ቸርነት ከተነበበ በኋላ በርካታ የምክር ቤት አባላት በዲያቆን ዳንኤል ክብረትና በአቶ ኦባንግ ሜቶ ላይ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በተለያዩ አጋጣሚዎች የሀይማኖት እውቀትን መሠረት በማድረግ ህዝብን ከህዝብ ጋር የሚያቀራርብ ሳይሆን የሚከፋፍል ንግግር ሲያደርግ እንደነበረ የጠቀሱ አንድ የምክር ቤት አባል ይህ ግለሰብ አሁን በዚህ የቦርድ አባልነት ውስጥ ተካቶ መቅረቡ ምክር ቤቱን መናቅ ነው ብለዋል፤ አንድ ሌላ የምክር ቤት አባል በበኩላቸው ዲያቆን ዳንኤል ከፋፋይ ንግሮችን በሀይማኖት መሀከል የሚያደርግ እንደሆነ ፀሀይ የሞቀው ጉዳይ እንደሆነ ገልፀወ፡ለቅ ቀደም ሲል ተሹሞ በነበረበት የፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባልነት ለመቀጠል አይመጥንም በማለት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፤
ሀገር የሚያፈርሱ ንግሮችን በማድረግና በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በማሰራጭት ከሚታወቁ ሰዎች መሀከል አንዱ ዲያቆን ዳንኤል መሆኑን የጠቀሱ ሌላ የምክር ቤት አባል ደግሞ ከእርሱ የተሻሉ ሰዎችን ለመሾም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምን እንዳልሞሩ ማብራሪያ ጠይቀዋል፡፡
አንዳንድ የምክር ቤት አባላት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቦርድ አባላትን ሲሰይሙ በራሳቸው መለኪያ ብቁ ሆነው ያገኙዋቸውን ሰዎችን እንደሆነ በመግለጽ ግለሰቦች ሊሳሳቱ ይችላሉ ያም ሆኖ በዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ የቀረቡት ቅሬታዎች በማስረጃ የተደገፉ እንዳልሆኑ የገለፁ ነበሩ፡፡
በዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ የቀረበው በርከት ያለ ተቃውሞን ከግምት ያስገቡት የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በዳንኤል ክብረት ላይ ብቻ የተለየ ውሳኔ አሳልፈን ወደ ድምፅ መስጠት ብንሄድ ይሻላል የሚል ሀሳብ አቅርበው ተቀባይነት ባማግኘቱ የምክር ቤቱ አባላት በዲያቆን ዳንኤል፤ ክብረት እጩነት ላይ ድምጽ እንዲሰጡ አድርገዋል፡፡
በዚህም መሠረት ዳንኤል ክብረት በእጩነት ሊቀርብ ይገባል በሚል 146 ድምፅ ሲሰጥ 129 አባላት ተወቃውሟቸውን ገልፀዋል፡፡ 29 አባላት ድምፀ ተአቅነቦ አድርገዋል፡፡ ነገር ግን ውጤቱን አፈጉባኤው እንደገለረፁ የሰጠነው ድምፅ በትክክል አልተቆጠረም ያሉ የምክር ቤት አባላት ተቃውሞ በማሰማታቸው በምክር ቤቱ የስነ ስርዓትና የአባላት ስነ ምግባር ደንብ ላይ በተደነገገው መሠረት በምክር ቤቱ በተሰጠ ድምጽ ላይ የቁጥር ለውጥ አለ ብሎ የሚጠይቅ የምክር ቤት አባል ካለ አፈ ጉባኤው ድጋሚ ድምፅ እንእንዲሰጥ እንደሚያደርጉ በመገለፁ በዲያቆን ዳንኤል ላይ ድጋሚ ድምፅ እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡
በዚህ ም መሠረት በሁለተኛው ዙር ድምጽ አሰጣጥ 148 ሰዎች ድጋፋቸውን ሲሰጡ 126 ተቃውሞ 24 ድምፅ ተአቅቦ ተመዝግቧል፡፡ በዚህ የቦርድ አባላት ሹመት ወቅት ከቀረቡት የቦርድ አባላት መሀከል አንዱ የሆኑ አቶ ኦባንግ ሜቶ ከዜግነት ጋር በተያያዘ ጥያቄ የቀረበባቸው ሲሆን የካናዳ ዜግነት ያላው ሰው በቦርድ አባልነት ሊሰራ ይችላል አይችልም የሚለው ጥያቄ ሳይመለስ ወደ ድምጽ መስጠት ስነ ስርዓት ተገብቶቷል፤ በቀረቡት ስምንት የቦርድ አባላት ላይ ድምጽ ተሰጥቶም በ28 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባላት ሆነው በመሰየም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መዕዛ አሸናፊ አማካይነት ቃለ መሀላ ሲፈፅሙ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በስፍራው አልተገኘም፡፡
ፓርላማው በዲ/ን ዳንኤል ክብረት ሹመት ሲጨቃጨቅ ዋለ
