የሴኔጋል ኮከብ አጥቂ ሳዲዮ ማኔ ፊፋ ኳታር ላይ በሚያዘጋጀዉ የዓለም ዋንጫ ላይ እንደማይሳተፍ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድኑ አረጋግጧል። ቡድኑ ይፋ እንዳደረገዉ ማኔ ከደረሰበት ጉዳት በማገገም ላይ ስለሆነ በዓለም ዋንጫ ላይ የብሔራዊ ቡድኑ አባል መሆን አይችልም።
ማኔ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ለጀርመኑ ባይር ሙንሽን ተሰልፎ ቨርደር ብሬመንን 6-1 ባሸነፈበት ግጥምያ ላይ ጉልበቱ ላይ ጉዳት ደርሶበት ቀዶ ጥገና ተደርጎለታል። በዚህም ምክንያት በዘንድሮዉ የዓለም ኳስ ግጥምያ መሳተፍ አልቻለም። የሳዲዮ ማኔ በኳታር በሚካሄደዉ የ 2022 የዓለም እግርኳስ ግጥምያ ላይ አለመሳተፍ በእግር ኳሱ ዓለም ከአገሩ ሌላ ለአህጉር አፍሪቃ ጉዳት ነዉ ይላሉ?

