የገንዘብ ሚኒስቴር በአዲሱ የጉምሩክ አዋጅ መሠረት፣ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ወይም ከጠቅላላው ጭነት 50% በላይ የኮንትሮባንድ እቃ የያዙ ተሽከርካሪዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲወረሱ የሚያዝ ረቂቅ መመሪያ አዘጋጀ።
ተደጋጋሚ ጥፋት ከተፈጸመ፣ ተሽከርካሪው ምስጢራዊ መደበቂያ (ሻግ) ካለው፣ ኬላ ከጣሰ ወይም እንደ የጦር መሳሪያና እጽ ያሉ የተከለከሉ ነገሮችን ከያዘ የእቃው ዋጋ ሳይታይ ወዲያውኑ ይወረሳል።
ቀላል ጥፋቶች ግን እንደ እቃው ዋጋ ከ100 ሺህ እስከ 300 ሺህ ብር በሚደርስ ቅጣት የሚታለፉ ሲሆን፣ ባለንብረቶች ከተጠያቂነት ለመዳን ከሾፌሮች ጋር ውል መፈራረም፣ ጂፒኤስ መግጠምና የተፈቀደ መስመር መጠቀም ይጠበቅባቸዋል።(ሪፖርተር)

