አሜሪካ ረቡዕ ዕለት በቀድሞው የኩባ ፕሬዝዳንት ራውል ካስትሮ ላይ የግድያ ወንጀል ክስ መመስረቷን አስታውቃለች ።
የ94 ዓመቱ ራውል ካስትሮ የአሜሪካ ዜጎችን ለመግደል በማሴር፣ በአራት የግድያ ወንጀል እና በሁለት አውሮፕላኖች ላይ በደረሰ አደጋ ክስ ቀርቦባቸዋል ።
ክሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኩባ ውስጥ የአገዛዝ ለውጥ እንዲደረግ የሚያደረጉት ጥረት አካል ነው ተብሏል ።
በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በኩባ በይፋ የታዩት ተከሳሹ በአሁኑ ጊዜ በምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳሉ አልተገለፀም ።

