ከጥቂት ቀናት በኃላ በሚደረገው ምርጫ 2013 በግል ይወዳደራሉ ተብለው ከሚጠበቁ ተወዳዳሪዎች መካከል ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በግል ምክንያት በምርጫው መቀጠል እንደማይችል አሳወቀ።
ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ይህ ያሳወቀው ዛሬ ለ’ጅማ ከተማ ነዋሪዎች’ በይፋዊ ማህበራዊ ገፃ ላይ ባሰራጩት አጭር የፅሁፍ መልዕክት ነው።
የኡስታዝ አህመዲን ጀበል ሙሉ መልዕክት ፦
“ዘንድሮ በሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጅማ ከተማ እንድወክላችሁ ሽማግሌ ከመላክ አንስቶ በተለያዩ መንገዶች እጩ እንድሆን በመጠየቅና ለእጩነት የሚጠበቀውን ፊርማ በራሳችሁ ተነሳሽነት በመፈረምና በማስፈረም የምርጫ ቅስቀሳ እንድጀምር፣ ለቅስቀሳውም «የሚጠበቅብንን ሁሉ ለመወጣት ከጎንህ ነን» በማለት ላሳደራችሁብኝ እምነትና አክብሮት ከልብ እያመሰገንኩ፤ በግል እጩነት ተመዘግቤ በነበረው በምርጫው በራሴ የግል ምክንያት ልቀጥል አለመቻሌን ላላሳወቅኳችሁ የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ሳሳውቃችሁ ከታላቅ አክብሮት እና ይቅርታ ጋር ነው”

