ኢትዮ ቴሌኮም በ2018 በጀት ዓመት 215.82 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

የኢትዮቴሌኮም የዳታ እና ኢንተርኔት አገልግሎት ገቢ ለመጀመሪያ ጊዜ ከድምፅ አገልግሎት በለጠ
ኢትዮ ቴሌኮም በ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ 215.82 ቢሊዮን ብር ገቢ በማመንጨት የዓመታዊ ዕቅዱን 99.7% ማሳካት ችሏል። የኢትዮ ቴሌ ኮም ዋና ስራአስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ እንደገለጹት ይህ ገቢ  ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ33.2% ዕድገት ማስመዝገብ ችሏል።
የዳታ እና ኢንተርኔት አገልግሎቶች ከጠቅላላ ገቢው 31.1% በመያዝ ኩባንያው ከተመሠረተበት ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ለሚሆን ጊዜ የድምፅ አገልግሎት የነበረውን ቀዳሚነት አስቀርተው ለመጀመሪያ ጊዜ የገቢው ዋነኛ አንቀሳቃሽ ሞተር መሆናቸው ተጠቁሟል።
እንደ ኩባንያዉ ሪፖርት ከሆነ፤ በበጀት ዓመቱ የሞባይል ድምፅ አገልግሎት 23.5% ድርሻ ሲይዝ፤ የተጨማሪ እሴት አገልግሎቶች 9.1%፣ ዓለም አቀፍ አገልግሎቶች 8%፣ የኢንተርፕራይዝ መፍትሄዎች 7.1% እንዲሁም ቴሌብር እና ሌሎች የዲጂታል ምርቶች ቀሪውን ድርሻ አበርክተዋል።
በተጨማሪም የኢትዮ ቴሌኮም ከዓለም አቀፍ አገልግሎቶች 139.9 ሚሊዮን ዶላር ጨምሮ በአጠቃላይ 188.48 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘቱ ተገልጿል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe