ከደቡብ ሱዳን የተሻገሩ የሙርሌ ታጣቂዎች ከጋምቤላ የኑዌር ህጻናትን ዳግም ሰረቁ

ከመቶ በላይ የቀንድ ከብትንም ዘርፈዋል፤

ከደቡብ ሱዳን ተሸግረው የመጡ የሙርሌ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን ጥቃት ማድረሳቸውን የጋምቤላ ክልል መንግስት አስታወቀ።

የጋምቤላ ክልል የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ አቶ ኡቶው ኡኮት ለዶይቼ ቬሌ እንደተናገሩት ከደቡብ ሱዳን የተሻገሩ የሙርሌ ጎሳ አባላት ሰሞኑን በጋምቤላ ክልል በኑዌርና አኙዋክ ዞኖች ህፃናትን ሰርቀዋል፤ እንስሳትን ዘርፈዋል፡፡ ትናንት ደግሞ በክልሉ ኑዌር ዞን አኮቦ ወረዳ ሰዎቸን ጭኖ ካንካን ከተባለ ቦታ ወደ ዋንቱዋ ሲጓዝ በነበረ የመንግስት መኪና ላይ የሩምታ ተኩስ ከፍተዉ ስምንት ሰዎችን ገድለዋል ብለዋል፤

ከተገደሉ ሰዎች በተጨማሪ  አምስት ሰዎችን ሲያቆስሉ፤ 101 ከብቶችን ዘርፈዋል ብለዋል።

በተሽከርካሪ ዉስጥ የመንግሥት አመራሮች እና ሰራተኞች እንዲሁም ነዋሪዎች እንደነበሩ የጠቀሱት አቶ ኡቶው፣ አሁን የፀጥታ ኃይል ስፍራዉ ላይ መሰማራቱን አመልክተዋል። መነሻቸው ደቡብ ሱዳን የሆነው የሙርሌ ጎሳ አባላት በየዓመቱ በጋምቤላ ክልል ህፃናትናና እንስሳትን በተደጋጋሚ እንደሚዘርፉ ይታወቃል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe