ከ2.5 ቢልየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው ሀይሌ ግራንድ አዲስ ባለ 5 ኮከብ ሆቴል በይፋ ስራ ጀመረ

በመዲናችን አዲስ አበባ በየካ ክፍለ ከተማ ላም በረት መናኽሪያ አካባቢ በ15 ሺህ ካ.ሜ ቦታ ላይ ያረፈውና ባለቤትነቱ የሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴ የሆነው የሀይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ስምንተኛ መዳረሻ ” ሀይሌ ግራንድ አዲስ አበባ ” ሙሉ በሙሉ ስራ መጀመሩ ዛሬ ተገልጿል።

2.5 ቢልየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት “ሃይሌ ግራንድ አዲስ አበባ” እ.ኤ.አ ከጥቅምት 01/2022 ጀምሮ በሙከራ ደረጃ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል።

ሆቴሉ ለ450 ሰራተኞች ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ለ120 #አዲስ_ተመራቂ ሰራተኞች ስልጠና በመስጠት ስራ እንዱጀምሩ መደረጉ ተገልጿል።

ሆቴሉ በውስጡ ፦

– 130 ክላሲክ ፤ 14 ስዊት ፤ 12 ፕሪሚየር እና 1 ፕሬዝዳንሻል ባጠቃላይ 175 አልጋዎችን የያዘ 157 ምቹና ሰፊ የመኝታ ክፍሎችን
– 4 ሬስቶራንቶች እና 2 PDR ፤
– 4 ባር፤
– 1pastery & coffe shop፤
– 1 የተሟላ የባህል ምግብ አዳራሽ፤
– 8 የስብሰባ አዳራሾች እና 2 ትላልቅ Ballrooms
– የጤና እና የውበት መጠበቂያ ማዕከል
– ጂም እንዲሁም 200 ተሽከርካሪዎችን የሚይዝ የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ይዟል።

ሆቴሉ የተገነባው በኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ብቻ መሆኑ የተነገረ ሲሆን በቀጣይ #ሐምሌ ወር ላይ #የወላይታ_ሶዶው ሆቴል እንደሚመረቅ፤ #የሻሸመኔው ሪዞርትም ጥገና ላይ እንዳለ ተገልጿል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe