የሩሲያ ወታደራዊ አውሮፕላን ተከሰከሰ፤ የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ

አውሮፕላኑ ከተነሳ ከጥቂት ጊዜ በኋላ የተከሰከሰ ሲሆን፣ በውስጡ ሰባት ሰዎች ተሳፍረውበት እንደነበር ተዘግቧል። እንደ አከባቢው መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ከሆነ ወደ ሆስፒታል በመወሰድ ላይ ሳሉ በደረሰባቸው ጉዳት ህይወታቸው ያለፈውን ሁለት ሰዎችን ጨምሮ የስድስት ሰዎች ሕይወት አልፏል።
የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴርን ጠቅሶ የሩሲያው ኢንተርፋክስ የዜና ወኪል እንደዘገበው፤ ማክሰኞ ዕለት በሩቅ ምስራቅ አሙር ክልል አንድ የሩሲያ ወታደራዊ አውሮፕላን ከተነሳ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ተከስክሶ የስድስት ሰዎች ሕይወት አልፏል።
በመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቶች መሠረት አውሮፕላኑ Tu-154) እንደሆነ ተለይቷል። አውሮፕላኑ በሶቪየት ዘመን የተሰራ ባለሶስት ሞተር ጄት ሲሆን፣ በመጀመሪያ ለመካከለኛ ርቀት የመንገደኞች ማጓጓዣነት የተነደፈ ቢሆንም የሩሲያ ወታደሮች እና መንግስት ለትራንስፖርት እና ለልዩ ተልዕኮዎች ሲጠቀሙበት ቆይተዋል። አውሮፕላኑ በውስጡ ሰባት ሰዎች አሳፍሮ ከተነሳ ከጥቂት ጊዜ በኋላ የተከሰከሰ ሲሆን፣ ወደ ሆስፒታል በመወሰድ ላይ ሳሉ በደረሰባቸው ጉዳት ህይወታቸው ያለፈውን ሁለት ሰዎችን ጨምሮ የስድስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ዘገባው አመልክቷል።
Tu-154 የመጀመሪያ በረራውን ያደረገው በ1968 እ.ኤ.አ (እ.ኤ.አ.አ) ሲሆን በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ ለንግድ በረራ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። በተለይም በሀገር ውስጥ የበረራ መስመሮች ላይ ከ1,000 በላይ አውሮፕላኖች ተመርተው በሶቪየት ህብረት ውስጥ በጣም በሰፊው ጥቅም ላይ ከዋሉ የመንገደኞች አውሮፕላኖች አንዱ ሆኖ ነበር።
የአውሮፕላኑ ታሪክ በርካታ ትኩረት የሳቡ ከወታደራዊ ዘርፍ ጋር የተያያዙ አደጋዎችም ተፈጥረዋል። በታህሳስ 2016 እ.ኤ.አ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር Tu-154 አውሮፕላን ሶቺ ከተማ ከተነሳ ከጥቂት ጊዜ በኋላ በጥቁር ባህር ውስጥ ተከስክሶ በውስጡ የነበሩት 92 ሰዎች በሙሉ ሕይወታቸው አልፏል። አውሮፕላኑ ወደ ሶሪያ በማመራት ላይ የነበሩ ወታደራዊ ሰራተኞችን፣ ጋዜጠኞችን አሳፍሮ ነበር።
በማክሰኞው አደጋ አውሮፕላኑ እንደተከሰከሰ የነዳጅ ታንከሩ በመፈንዳቱ ፍርስራሹ ላይ እሳት ተነስቷል። ባለስልጣናት አውሮፕላኑ እንዲከሰከስ ያደረገውን ምክንያት እስካሁን ይፋ ያላደረጉ ሲሆን፣ ስለ አደጋው መንስኤ ምርመራ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe