ወላጅ፦ “ወንድምኽን ለምን ገፋኽው?”
ልጅ፦ “ስላላነደደኝ ገፋኹት”
ወላጅ፦ ” ምን አድርጎኽ ነው?”
ልጅ፦ “አላውቅም” “I don’t know”
……………………………..
ወላጅ፦ “የእህትሽን እቃ ለምን ወረወርሽ?”
ልጅ፦ “ስላበሳጨችኝ ወረወርኩ”
ወላጅ “ለምን?”
ልጅ፦ “አላውቅም” “I don’t know”
የብዙ ወላጆችን ትዕግስት የሚፈታተነው የልጆች ምላሽ “አላውቅም” የሚለው ቃል ሲወጣ ነው። ይኹንና ልጆች በአብዛኛው እድሜያቸው ከ12 አመት በታች ያሉ ይኽንን ቢሉ ትክክል ናቸው። አልዋሹንም ፣ ጥያቄውን ለመጠምዘዝም አስበው አይደለም። ታዲያ ምንድነው ካልን Adulthood bias
Adulthood bias የሚባለው አዋቂዎች የልጅነት ሕይወት ምን እንደሚመስል የመርሳት አዝማሚያ ነው።
ልጅ ኾነን አሳለፍን ካበቃን በኃላ የልጅነትን ሕይወት መርሳትን ይመለከታል። ስውሩ የወላጅነት ትግል ተብሎ የሚጠራው Adulthood bias ልጅን እንደልጅነቱ አለመቀበልና እንደአዋቂ እንዲያስቡ መጠበቅን ያካትታል።
እድሜያቸው ከ12 አመት በታች ያሉ ሕጻናት በአመክንዮ (Reasoning) ሳይኾን ለነገሮች ስሜትን መሰረት ያደረገ ምላሽ ይሰጣሉ።
በጽሑፌ መግቢያ ላይ የወላጆች ጥያቄ ምላሽ የሚፈልገው ምክንያት ቢኾንም የልጆች ምላሽ ግን ስሜታቸውን ነው የገለጹት፤ “ስላናደደኝ” ” ስላበሳጨኝ” የሚሉ ናቸው።

በዚኽ የእድሜ ክልል የሚገኙ ልጆች የሚሰጡት ምላሽ ስሜታዊነትን ማዕከል ያደረገ ነው። Adulthood bias ደግሞ ልጆችን እንደአዋቂ በምክንያትነት እንዲያብራሩ ይጠብቃል።
Adulthood bias መፍትሄ
ልጆችን እንደአዋቂ እንዲያስቡ ከመጠበቅ መቆጠብና ለልጆች ስሜት እውቅና መስጠት (Emotional Validation) ይመከራል።
የተናደደን ልጅ ለምን ተናደድክ አንተ/ቺ እንዲህና እንዲያ ከማለት ይልቅ የሚያበሳጭ ነገር ገጥሞኽ መናደድህን መረዳት ችያለኹ፤ አኹን ከጎንኽ ነኝ ብሎ ለስሜቱ እውቅና ሰጥቶ ማረጋጋት ይጠበቃል።
ለስሜቱ እውቅና ያገኘ ልጅ ከስህተቱ ለመማር ዝግጁ የመኾን እድሉ ሰፊ ነው። (Teachable moment)
የልጆችን የእድገት ሂደት መረዳት ይገባል።
መደምደሚያ
ልጆችን በማወቅም ኾነ ባለማወቅ እንደአዋቂ እንዲያስቡ ከመጠበቅ ወጥመድ በመላቀቅ ከእነሱ አመክንዮ ሳይኾን ስሜቶቻቸውን እየተረዳን እንከባከባቸው መልዕክቴ ነው።
ብርሃኑ በላቸው አሰፋ

