የናይጄሪያ አጠቃላይ የውጭ ዕዳ በ2025 መጨረሻ ወደ 145 ቢሊዮን ዶላር ማደጉን የዓለም ባንክ አስታውቋል ። የዕዳው መጠን በ2024 ከነበረው 135 ቢሊዮን ዶላር በ6.6 በመቶ ጨምሯል።
በዓለም ባንክ የ2026 ዓለም አቀፍ የዕዳ ስታቲስቲክስ ሪፖርት መሠረት፣ የተጠቀሰው አሃዝ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ የተወሰዱ የውጭ ብድሮችን ያካትታል።
ባንኩ እየጨመረ የመጣው የብድር ወለድና የክፍያ ወጪ በታዳጊ ሀገራት ላይ የፋይናንስ ጫና እየፈጠረ እንደሚገኝ ገልጿል ።
በዚህም ለጤና፣ ለትምህርትና ለሌሎች መሠረታዊ አገልግሎቶች የሚመደበውን በጀት እየገደበ መሆኑን አስጠንቅቋል።
በአጠቃላይ የታዳጊ ሀገራት የውጭ ዕዳ በ2025 በ5.5 በመቶ በማደግ 9.4 ትሪሊዮን ዶላር መድረሱን ሪፖርቱ አመልክቷል።

