የአቃቂ ቃሊቲ ወንዝ የ8 እና የ12 ዓመት ልጆችን ህይወት ቀጠፈ

የህፃናቱን ሕይወት የቀጠፈው ወንዝ፣ ክረምት በመጣ ቁጥር የወላጆች ስጋት ነው

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 10 በተለምዶ ሳሪስ ቀይ አፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አቋርጦ የሚያልፈው የአቃቂ ቃሊቲ ወንዝ ተፋሰስ ከዓመት በፊት አብዱልከሪም ኸይሩ እና ትንሳኤ ጌታቸው የተባሉ የ8 እና የ12 ዓመት ልጆችን ህይወት ቀጥፏል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በክስተቱ እጅግ አዝነው ወንዙ ዳግም ጉዳት እንዳያስከትል በሚል የጎርፍ መከላከያ ግድብ እንዲሰራላቸው ለከተማ አስተዳደሩ ተደጋጋሚ ጥያቄ ማቅረባቸውን ለኢቢሲ ሳይበር በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።

አካባቢውን እና በአካባቢው የሚገኘውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ከጎርፍ አደጋ ለመከላከል የጎርፍ መከላከያ ለመስራት ኢኮስኮ በተባለ የኮንስትራክሽን ድርጅት ግንባታው ተከናውኖ የነበረ ቢሆንም በጥራት ጉድለት የታለመለትን አገልግሎት ሳይሰጥ መፍረሱን የአካባቢው ነዋሪ አቶ ተስፋዬ ፀጋዬ ይገልፃሉ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe