አርቲስት ዳዊት ፍሬው ለሙዚቃ ስራ ወደ ጣሊያን ሀገር ተጉዞ ነበር።ክላርኔት ተጫዋቹ እና ሙዚቀኛው ዳዊት ህይወቱ አልፎ የተገኘው #በተኛበት_ክፍል መሆኑና የጣሊያን ፖሊስ የአሟሟቱን ሁኔታ እያጣራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በጣሊያን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና የሞያ አጋሮቹ ከሀገሪቱ ፖሊስ ጋር ተነጋግረው የአርቲስቱን አስክሬን በሀገሩ ለመላክ ችለዋል።
ዳዊት ፍሬው የክላርኔት የሙዚቃ መሳሪያውን እየተጫወተ የሰራው ሶስት የሙዚቃ አልበም ያለው ሲሆን የአንጋፋው ድምፃዊ ፍሬው ሀይሉ ልጅ ነው።
ከአርቲስት ዳዊት ፍሬው ስራዎች መካከል አንዱ ” ጥላ ከለላዬ ” የተሰኘው በመሳሪያ የተቀነባበረ መዚቃ ሲሆን በዚሁ ስራ ይህ ስንኝ ይገኝበታል። በሙዚቃ መሣሪያ ብቻ በተቀነባበሩት የሙዚቃ አልበሞቹ ላይ አንጋፋው አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያምና አርቲስት ተፈሪ ዓለሙን የመሳሰሉ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ሲሆን አንጋፋው የሙዚቃ መምህርና ባለሙያ ፈለቀ ኃይሉ ያቀናበራቸው ናቸው፡፡
ታዋቂው የክላርኔት የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋች፤ ሙዚቀኛ ዳዊት ፍሬው መስከረም 7 ቀን 1971 ዓ.ም በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ ደጃች ውቤ ሠፈር ተወለደ፡፡
ሙዚቀኛ ዳዊት ፍሬው የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በራስ አበበ አረጋይ ትምህርት ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በእንጢጦ አጠቃላይ ከአጠናቀቀ በኋላ ከልጅነቱ ጀምሮ በውስጡ ይመኘው የነበረውን የሙዚቃ ትምህርት ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት የሙዚቃ ትምህርቱን አጠናቆ ተመርቋል፡፡
ሙዚቀኛ ዳዊት ፍሬው በዋነኛነት ከሚታወቅበት የክላርነቴ የሙዚቃ መሳሪያ በተጨማሪ አልቶ ሳክስፎን፣ ክራር የሙዚቃ መሳሪያዎችን ይጫወታል፡፡
ሙዚቀኛ ዳዊት ፍሬው አራት የሙዚቃ መሳሪያ የተቀነባበሩ የሙዚቃ አልበም ለህዝብ አቅርቧል ፡፡
በተጨማሪም ከአዲስ አኩስቲክ ባንድ ጋር በነበረው ቆይታ ትውስታ ቢል ርዕስ በተዘጋጀ አልበም ላይ ያለውን በቃት በማሳያቱ የተለያዩ የውጭ ሀገር ሚዲያ ስላለው የኢትዮጵያ ዜማዎች በኢትዮጵያ ቅላፄ አጨዋወት መስክረውለታል፡፡
ዳዊት በሙያው በመላው ኢትዮጵያ ተዟዙሮ ስራዎችን ከማቅረቡ በላይ ከሀገር ውጪ በፈረንሳይ፣ ጀርመን ዴንማርክ፣ ሲዊድን፣ ሆላንድ ኳታር፣ ለንደን፣ ጅቡቲ ተዘዋውሮ ስራዎቹን አቅርቧል፡፡
ሙዚቀኛ ዳዊት ፍሬው በኢትዮጵያ ቀደምትና የመጀመሪያ ከነበሩ ድምፃዊያን መካከል የታዋቂው ድምፃዊና ሙዚቀኛ የፍሬው ኃይሉ ልጅ ሲሆን ወደ ሙያው ለመምጣት የአባቱ ተፅእኖ ቀላል እንዳልሆ ይናገራል፡፡

