የውጭ ባንኮች መግባት (Foreign Bank Entry) መንግስት የባንክ ዘርፉን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ማድረጉ፣ የአገር ውስጥ ባንኮችን ትልቅ ስጋት ላይ ሸየጣላቸው እንደሆነ ይነገራል፡፡
እንደ ኬኒያ ንግድ ባንክ ( KCB) እና ሌሎች ያሉ ትላልቅ የውጭ ባንኮች በቴክኖሎጂ፣ በካፒታል እና በልምድ በልጠው ስለሚመጡ፣ የአገር ውስጥ ባንኮች እራሳቸውን በፍጥነት ካላስተካከሉ ከገበያው ሊወጡ ይችላሉ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባንኮች ሊኖራቸው የሚገባውን ዝቅተኛ የተከፈለ ካፒታል ወደ 5 ቢሊዮን ብር ከፍ ማድረጉ ይታወሳል። ብዙዎቹ ትናንሽ እና መካከለኛ ባንኮች ይህንን መስፈርት ለማሟላት እየተጋደሉ ነው። ካፒታሉን ማሟላት ያልቻሉ ባንኮች የመዋጥ (Merger) ወይም የመክሰር አደጋ ተጋርጦባቸዋል። አሁንም ብዙ ባንኮች በቂ ጥሬ ገንዘብ በእጃቸው የማቆየት ችግር ያለባቸው ሲሆን በተለይ ብሔራዊ ባንክ የሚከተለው የገንዘብ ቁጥጥር ፖሊሲ እና የብድር ገደብ ባንኮቹ ብድር ሰጥተው እንዳያተርፉ አጣብቂኝ ውስጥ እንደከተታቸው ይነገራል፡፡
በአጠቃላይ ባንኮቹ የቆየው አሰራራቸው (ባህላዊ የብድር አሰጣጥ፣ አነስተኛ ቴክኖሎጂ እና አነስተኛ ካፒታል) ከአሁን በኋላ ሊያስኬዳቸው የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል ማለት ነው።
ከዚህ ገደል ላለመውደቅ፦ ካፒታላቸውን ማሳደግ፣ በቴክኖሎጂ መዘመን፣ እና አዳዲስ የገቢ ምንጮችን መፈለግ ይኖርባቸዋል እንላለን።
የውጭ ባንኮች መግባት (Foreign Bank Entry)

