የ4 ዓመት ከ9 ወር ህፃን አግቶ ገንዘብ የጠየቀው ግለሰብ በፖሊስ ተያዘ።

የ4 ዓመት ከ9 ወር ዕድሜ ያላትን ህጻን ልጅ ከትምህርት ቤት አግቶ በመውሰድ ገንዘብ የጠየቀው ግለሰብ የአዲስ አበባ ፖሊስ አደረኩት ባለው ክትትል ከአዲስ አበባ ውጪ በቁጥጥር ሥር እንደዋለው ግልጿል።

የእገታ ወንጀሉ የተፈፀመው ሰኔ 29 ቀን 2013 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 10 ሰዓት ተኩል ገደማ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ነው።

ተጠርጣሪው ግለሰብ የህፃኗ ወላጆች ንብረት በሆነ ሆቴል ለ2 ዓመታት ያህል በጥበቃ ሰራተኝነት እያገለገለ የቆየ ሲሆን በዕለቱ ህፃኗን ከምትማርበት ት/ቤት እንዲያመጣት በወላጆቿ ሲታዘዝ እሱ ግን የታዘዘውን ወደ ጎን በመተው ህፃኗን ይዞ ይሰወራል።

በኃላም ወላጆቿ ጋር በመደዋ ልጃችሁን አግቻታለሁ 250 ሺህ ብር አዘጋጁ ካለበለዚያ አታገኟትም የሚል ማስፈራሪያ በስልክ ያደርሳቸዋን።

ወላጆችም ድርጊቱን ለፖሊስ ሪፖርት ያደርጋሉ፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ የክትትልና ኦፕሬሽን ክፍል የህፃኗ መጥፋት ሪፖርት ከደረሰው ሰዓት ጀምሮ ተጠርጣሪውን የማፈላለግ ስራ ሲሰራ ቆይቶ በታገተች በ2ኛው ቀን ሃምሌ 01/ 2013 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ፍቼ ከተማ ውስጥ ህፃኗን ይዞ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ስር ሊውለው ችሏል።

በተጠርጣሪው ላይ ምርመራ እየተጣራ መሆኑንም የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

SourceENA

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe