ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ለንደን ሄትሮ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ አዳልጦት በመውደቁ ወለም እንዳለው ታወቀ፡፡
ተወዳጁ ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ በሀገረ እንግሊዝ የነበረውን የሙዚቃ ኮንሰርት አጠናቆ ተላንት ጠዋት ወደ ሀገሩ ሲመለስ ሄትሮ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ አዳልጦት በመውደቁ ወለም ብሎታል፡፡
አርቲስት ጎሳዬ ወደ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ወለምታው አላራምድ ስላላው በዊልቼር ላይ ተቀምጦ ወደ ቤቱ ለመሄድ መገደዱን ታዲያስ አዲስ ዘግቧል።
በአሁኑ ሰዓት ጎሳዬ ህክምናውን በቤተሳይዳ ሜዲካል ሴንተር እየተከታተለ ሲሆን ከአንድ ወር በኋላ ወደ ስራው ሙሉ ለሙሉ እንደሚመለስ ታውቋል፡፡

