1 የአሜሪካ ዶላር በኢራን 42,125 የኢራን ሪያል መመንዘሩ ተቃውሞ ቀሰቀሰ

1 የአሜሪካ ዶላር በ 42,125 የኢራን ሪያል መመንዘሩን ተከትሎ ተቃውሞ ቀሰቀሰ

በኢራን ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ
​በኢራን የሀገሪቱ ገንዘብ (ሪያል) ከዶላር ጋር ሲነፃፀር ታሪካዊ የተባለ ዝቅተኛ ውድቀት ማሳየቱን ተከትሎ፣ ላለፉት ሶስት አመታት ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ በመላ ሀገሪቱ ተቀስቅሷል።
​
​የገንዘብ ውድቀት፦ የኢራን ሪያል ዋጋ በአስገራሚ ሁኔታ ማሽቆልቆሉን ቀጥሏል። በአሁኑ ሰዓት 1 የአሜሪካ ዶላር በ 42,125 የኢራን ሪያል  እየተመነዘረ ይገኛል።

​የገበያ መዘጋት፦ በዋና ከተማዋ ቴህራን የሚገኙ የሞባይል ስልኮች መሸጫ ማዕከላትና ታሪካዊው “ግራንድ ባዛር” ነጋዴዎች ሱቆቻቸውን በመዝጋት አደባባይ ወጥተዋል።

​የባንክ ሹሙ መልቀቂያ፦ የኢኮኖሚ ቀውሱንና ህዝባዊ ቁጣውን ተከትሎ የኢራን ማዕከላዊ ባንክ ገዢ መሀመድ ረዛ ፋርዚን ሰኞ (ታህሳስ 20 ቀን 2018 ዓ.ም / Dec 29, 2025) ስልጣናቸውን መልቀቃቸው ተሰምቷል።

​የፖሊስ እርምጃ፦ በቴህራን፣ ኢስፋሃን፣ ሺራዝ እና ማሽሃድ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች የቀጠሉ ሲሆን፣ ፖሊስ ሰልፈኞቹን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ እየተጠቀመ መሆኑ ተዘግቧል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe