(1) 33ኛው ኦሊምፒክ ነው
(2) አርብ ሀምሌ 19 ይጀመርና እሁድ ነሀሴ 5 ይጠናቀቃል
(3) በ32 ስፖርቶች 329 የሜዳሊያ ውድድሮች ይካሄዳሉ
(4) 10,500 ስፖርተኞች ከ206 ሀገራት ይሳተፋሉ
(5) 20ሺህ ጋዜጠኞች ከቦታው ይዘግባሉ
(6) 45ሺህ በጎ ፈቃደኞች በኦሊምፒኩ ያገለግላሉ
(7) ከ45ሺህ በላይ የፀጥታ ሀይሎች ተመድበዋል
(8 39 የመወዳደሪያ ቦታዎች በ16 ከተሞች ተዘጋጅተዋል
(9) የመክፈቻው ስነ ስርአት የመግቢያ ዋጋ ትንሹ 90 ትልቁ 2,700 ዶላር ነው
(10) የሌሎች ቀናት ትኬት ከ24 እስከ 980 ዶላር ሆኗል
(11) 10 ሚሊየን ትኬት ተዘጋጅቷል፤ እስካሁን 9 ሚሊየኑ ተሸጧል
(12) እስካሁን የ197 ሀገራት ዜጎች ትኬት ገዝተዋል፤ ከፈረንሳዊያን ውጪ የብሪታኒያ፣ አሜሪካ፣ ጀርመንና ሆላንድ ዜጎች ብዙ ትኬት የቆረጡ አራት ሀገራት ሆነዋል
(13) ፓሪስ ከ100 አመት በኋላ ኦሊምፒክን ታዘጋጃለች
(14) በ1900 እና 1924 አዘጋጅታ ነበር፥ ይህ 3ኛዋ ነው
(15) ፈረንሳይ ለዚህ ኦሊምፒክ 9 ቢሊየን ዶላር በጀት መድባለች
(16) ከቶኪዮ ሶስት እጥፍ ያነሰ ከሲዲኒ በኋላም ዝቅተኛ ወጪ ሆኗል፤ ምክንያቱ ደግሞ ብዙዎቹ መሰረተ ልማቶች ቀድመው የተሰሩ በመሆናቸው ነው ተብሏል
(17) 54 ሄክታር ላይ ያረፉ ሶስት የኦሊምፒክ መንደሮች ተገንብተዋል
(18) 12 የላውንደሪ ክፍሎችና 600 የማጠቢያ ማሽኖች ተገጥመዋል፤ 20 የውበት መጠበቂያ ሳሎኖች አሉ
(19) በኦሊምፒክ መንደሩ 16ሺህ አልጋዎች ተዘርግተዋል
(20) በመንደሩ 300ሺህ ኮንዶሞች ተቀምጠዋል
(21) 13 ሚሊየን ምግብ ፓሪስ ለስፖርተኞቹ ታቀርባለች፤ 3 ሚሊየን ሙዝ፣ 36ሺህ ኪሎ ቡና ይገኝበታል፤ 80% ፈረንሳይ የተመረቱ ናቸው
(22) ከ4 ቢሊየን ክዝብ በላይ ኦሊምፒኩን ይመለከተዋል ተብሎ ይጠበቃል፤ 350ሺህ ሰዓት የቴሌቪዥን ሽፋን ይኖረዋል
(23) በኦሊምፒክ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የአለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ለአሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማት አዘጋጅቷል፤ 2.4 ሚሊየን ዶላር መድቧል፤ ወርቅ የሚያጠልቁ አትሌቶች 50ሺህ ዶላር ያገኛሉ
(24) አሜሪካ 592 ስፖርተኞችን ወደ ፓሪስ በመላክ በቁጥር ቀዳሚ ስትሆን አራት ሀገራት አንድ አንድ አትሌቶችን በመላክ የመጨረሻውን ይዘዋል
(25) አሜሪካ 314 ሴቶችን በማሳተፍ ቀዳሚ ስትሆን ሶማሊያና ኢራቅን ጨምሮ ስድስት ሀገራት የሴት ተሳትፎ የላቸውም
(26) አሜሪካዊው ዋናተኛ ማይክል ፊሊፕስ ለ5ኛ ጊዜ ኦሊምፒክ በመሳተፍና 28 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ብቸኛው ስፖርተኛ ሆኗል
(27) 35 አትሌቶች በተለያዩ ስፖርቶች ስደተኞችን ወክለው ይወዳደራሉ፤ አብዛኞቹ ከሶሪያ፣ አፍጋኒስታንና ኢራን ሲሆኑ ኢትዮጵያዊቷ እየሩ ገብሩ በብስክሌት ትሳተፋለች
(28) ከቤልጂየም ፓሪስ 263ኪ.ሜ ወይም የሶስት ሰዓት የመኪና መንገድ ነው፤ አጭር ተጓዥ ቤልጂየም ነች፤ ከኒውዝላንድ ፓሪስ 18,500 ኪ.ሜ ወይም የሙሉ ቀን በረራ ይፈጃል፤ ረጅሟ ተጓዥ ኒውዝላንድ ነች
(29) 12 ሚሊየን ጎብኚ ኦሊምፒኩን መሰረት አድርጎ ፓሪስ ይመጣል ተብሎ ይጠበቃል
(30) 5,084 ሜዳሊያዎች ተመርተዋል፤ የወርቁ 529 ግራም፣ የብሩ 525 ግራም እንዲሁም ነሀሱ 455 ግራም ይመዝናሉ
(31) ሜዳሊያዎቹ ከኤፈልታወር ከተቆረጠ 18 ግራም ብረት የሚሰሩ ሲሆን እንደ ደረጃቸው ወርቅ፣ ብርና ነሀስ ይለጠፍባቸዋል
(32)የፓሪስ ኦሊምፒክ ለ150ሺህ ሰው የስራ እድል ፈጥሯል
(33) ሳምሰንግ አዲስ ምርቱን ጋላክሲ ዜድን በኦሊምፒኩና በፓራኦሊምፒኩ ለሚሳተፉ 17ሺህ ስፖርተኞች በነፃ ያድላል
★ የኦሊምፒክ ዘገባዎቼ በህይወት ላጣናቸው ጋዜጠኞች ገነነ መኩርያ(ሊብሮ) እና መሸሻ ወልዴ መታሰቢያ ይሁንልኝ!
(ታምሩ ዓለሙ)

