35 አገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በ ” አስቸኳይ የሰላም ጥሪ ” ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይሰጡ ታገዱ

በኢንተር ላግዤሪ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠጥ ጋዘጠኞችን ጠርተው የነበሩት 35 አገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መግለጫውን እንዳይሰጡ ፀጥታ ሀይሎች ቢታገዱም ዛሬ ባወጡት መግለጫ በኢትዮጵያ ጦርነት እና ግጭቶች ቆመው፣ ሐቀኛ፣ ሰላማዊና የግጭቶቹ ተሳታፊ አካላትን በሙሉ ያካተቱ የእርቅ ንግግሮች እንዲጀመሩ ጠይቀዋል።

ጦርነት እና ግጭት ህዝቡን በብዙ መልኩ ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለ ነው ያሉት ድርጅቶቹ በአዲሱ አመት ያሉ ችግሮች ተቀርፈው ለማየት መፍትሄ ናቸው ያሏቸውን ሃሳቦች አቅርበዋል።

– በትግራይ፣ አማራና አፋር ክልል ያለው ጦርነትና በሌሎችም አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች በአስቸኳይ ቆመው፣ ሐቀኛ፣ ሰላማዊና የግጭቶቹ ተሳታፊ አካላትን በሙሉ ያካተቱ የእርቅ ንግግሮች እንዲጀመሩ፤

– በትግራይና ጦርነት ባለባቸው አካባቢዎች ሁሉ የተቋረጡ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች በአፋጣኝ እንዲጀመሩና ዕርዳታ ያለ እንቅፋት እንዲደርስ፤

– የፆታ ጥቃትን የፈፀሙ የተዋጊ አካላትን ጨምሮ ሌሎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ያደረሱ አካላት ላይ ተጨማሪ ምርመራ ተደርጎ እርምጃ እንዲወሰድ፤

– ብሔር ተኮር ጥቃቶችና አግላይ ድርጊቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ። በፌዴራሉ እና ክልል መንግሥታት በቁጥር አነስተኛ ለሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች እና ግፉዓን ዜጎች የልዩ ጥበቃ ስርዓት እንዲዘረጋ፤

– ተፋላሚ አካላትና ደጋፊዎቻቸው ከማንኛውም የጦርነት ፕሮፓጋንዳና የግጭት አባባሽ ንግግሮች እና ድርጊቶች እንዲቆጠቡ፤

– በአገር ውስጥ ሆነ በውጭ ያሉ መገናኛ ብዙኃን፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ የእምነት ተቋማት፣ የፖለቲካ ኃይሎችና አክቲቪስቶች ድምፃቸውን ለሰላምና ለእርቅ ብቻ እንዲያውሉ፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe