37 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን መሠረታዊ የውሃ አገልግሎት የላቸውም ሲል አዲስ ጥናት አመለከተ

በቅርቡ ይፋ የሆነው የዓለም ጤና ድርጅት እና የዩኒሴፍ የጋራ ጥናት እንደሚያሳየው፣ በኢትዮጵያ ውስጥ 37 ሚሊዮን ሰዎች መሠረታዊ የውሃ አገልግሎት አያገኙም። ይህ አኃዝ አገሪቷን በአፍሪካ ውስጥ ዋነኛ የውሃ ችግር ካለባቸው ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ አድርጓታል።
ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው፣ ምንም እንኳን በገጠር አካባቢዎች የንፁህ ውሃ አቅርቦት በ2000 ከነበረው 14% ወደ 71% በ2024 ከፍ ቢልም፣ በከተሞች ግን ዕድገቱ በሚጠበቀው ልክ አይደለም ብሏል።
በተጨማሪም፣ በፖለቲካዊ አለመረጋጋት እና በሀብት እጥረት ምክንያት የውሃ፣ ንጽህና እና ሳኒቴሽን አገልግሎቶችን የማስፋፋት ሥራው ፈተና እንደገጠማት ጥናቱ አመልክቷል።
በዚህ ሪፖርት ውስጥ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የወር አበባ ንጽህና መረጃም ተካቷል። ይህ መረጃ አብዛኞቹ ሴቶችና ልጃገረዶች የወር አበባ ማጽጃ ቁሳቁሶችን የሚጠቀሙ ቢሆንም፣ በቂ አቅርቦት ባለመኖሩ የጤናና ማህበራዊ ችግሮች እንደሚያጋጥሟቸው አስረድቷል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe