5ቱ የቦብ ማርሌይ ልጆች የሚሳተፉበት የሙዚቃ ድግስ በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው

 5ቱ የታዋቂው የሬጌ ንጉስ የቦብ ማርሌይ ልጆች የሚሳተፉበት የሙዚቃ ድግስ በኢትዮጵያ ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ።
ትኩረቱን ሰላም ላይ ያደረገ የሙዚቃ ድግስ በኢትዮጵያ ሊካሄድ መሆኑን ድምጻዊ ዘለቀ ገሰሰ ገለጸ፡፡
የሙዚቃ ድግሱን ከሚያዘጋጁት መካከል አንዱ የሆነው ድምጻዊ ዘለቀ ገሰሰ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረገው ቆይታ “ዋን ላቭ” የተሰኘ የሰላም የሙዚቃ ድግስ ለማካሄድ ዝግጅት መጀመሩን ተናግሯል።
በመጭው ግንቦት ወር ሊካሄድ የታቀደው ይህ ታላቅ የሙዚቃ ድግስ 5ቱን የቦብ ማርሌይን ልጆች ማለትም ዚጊ ማርሌይ፣ ስቴፈን ማርሌይ፣ ጁሊያን ማርሌይ፣ ዳሚያን ማርሌይ እና ኪማኒ ማርሌይ ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ተሳታፊ እንደሚያደርግ ነው የገለጸው።
ከዚህም ባሻገር ከኬንያ ሩዋንዳ ታንዛንያ እንዲሁም ከደቡብ አፍሪካ የተውጣጡ ድምጻውያንም በሙዚቃ ድግሱ እንደሚሳተፉ ተጠቅሷል፡
ዝግጅቱ ሰላም ፍቅርና አንድነት ላይ ያተኮረ ነው ያለው ድምጻዊው ዘለቀ ገሰሰ ከኢትዮጵያ ባሻገር በአፍሪካ
የተለያዩ አካባቢዎች ያለውን ውጥረት ለማቅለልና ሰላም እንዲፈጠር የማድረግ መንፈስ የያዘ ስለመሆኑ ነው
የገለጸው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe