በአቃቂ ክፍለ ከተማ ከዕድሜ ብዛት ሊፈርሱ የተቃረቡ ከእንጨት፣ ቆርቆሮ እና ጭቃ የተሰሩ ቤቶችን ሃይንከን ኢትዮጵያ አፍርሶ እያንዳንዱ ክፍል 30 ካሬ ስፋት እንዲኖረዉ አድርጎ በመስራት ባለ አንድ ፎቅ ህንጻ ለነዋሪዎቹ መልሶ አስረክቧል። ህንጻው ደረጃችዉን የጠበቁ የመታጠቢያ፣ የመጸዳጃ እና የማብሰያ ከፍሎችን ያካተተ ሲሆን 16 አባወራዎችን ከእነ ቤተሰቦቻቸው የያዘ ነው፡፡
እስካሁን ድረስ ሃይኒከን ኢትዮጵያ በዋልያ ቢራ ስያሜ አራት የደራሽ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት፣ በቀላል መንገድ እና በታማኝነት አከናውኗል። ባለፉት ሶስት ዓመታትም በልደታ ክፍለ ከተማ ከረዩ ሰፈር፣ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ቀጨኔ ላይ እና በጨርቆስ የገነባቸውን 145 ደረጃቸውን የጠበቁ መኖርያ ቤቶች ለነዋሪዎች ማስረከቡ ይታወሳል።
የሃይንከን የውጭ ግንኙነት ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍቃዱ በሻህ እንደገለፁት፤ ሃይንከን በመጪው ዓመት ሌሎቸ አካባቢዎች ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ የሚኖሩ ወገኖችን ለመርዳት አቅዷል።

በመዲናችን አዲስ አበባ ደረጃችዉን ያልጠበቁና ያረጁ ቤቶች እንደ ሌሎቹ የአፍሪካ ሃገራት ሁሉ በብዛት ይገኛሉ፡፡ ቤቶቹ ያረጁ፣ የተበታተኑ እና ቤተሰብን ለማስተናገድ በጣም ጠባብ እንዲሁም ለጤና ችግሮች ሊያጋልጡ የሚችሉ ነበሩ። በእነዚህ አካባቢዎች በሚገኙ ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ አብዛኛዎቹ ቤተሰቦች ከደረጃ በታች የሆኑ መጸዳጃ ቤቶችን ይጋራሉ።
የኢትዮጵያ መንግስት በተለያዩ ምክንያቶች በዋናነት ደግሞ በስነ-ሕዝብ ለውጥና በሕዝብ ፋይናንስ ላይ በሚደርስ ጫና ሁሉንም ያረጁ ቤቶችን በአንድ ጊዜ ማደስ አልቻለም።
ይህንን በመረዳት ሃይንከን ኢትዮጵያ በ2019 እኤአ የደራሽ ቤቶችን ፕሮጀክት ጀምሯል፡፡ ይህም ማህበራዊ ዘላቂነት ላይ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው። የደራሽ ፕሮጀክት በኢኮኖሚ ከተቸገሩ ወገኖች ጋር በመቆም በዋናነት የአገሪቱን ሁለት ዋና ዋና ተግዳሮቶች ለመፍታት ማለትም ለተቸገሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ደረጃውን የጠበቀ መኖሪያ ቤት ለማቅረብ እና የግንባታ ሥራዎችን ለመፍጠር ያለመ ነው።

