ለ12ኛ ክፍል ፈተና ከ80ሺ በላይ ኮምፒውተሮች እየተዘጋጁ እንደሆነ ተገለጸ

ዘንድሮ በበይነ መረብ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ80ሺ በላይ ኮምፒውተሮች እየተዘጋጁ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

ለ2ኛ ጊዜ በበይነ መረብ ለሚሰጠው የ12ኛ ከፍል መልቀቂያ ፈተና ከ80ሺ በላይ ኮምፒውተሮች እየተሰናዱ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዘንድሮ ለፈተናው ከሚቀመጡት 608ሺ በላይ ተማሪዎች 150ሺ ያህሉን በበይነ መረብ ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡ ፈተናው ባለፈው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በበይነ መረብ የመፈተኛ ኮምፒውተሮች እጥረት እንደነበር ተቋሙ ገልጻል፡፡

ችግሩን ለመፍታት ጥረት በማድረግ ከሰኔ 23 እስከ ሀምሌ 8 ለሚሰጠው የዘንድሮው ፈተና ከ80ሺ በላይ ኮምፒውተሮች እየተዘጋጁ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ልጆቻቸውን በግል ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ ወላጆች በራሳቸው ፈቃድ የመፈተኛ ኮምፒውተሮችን በድጋፍ መልክ ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል፡፡

ተማሪዎች አስቀድመው በበይነ መረብ ለመፈተን የሚያስችል ልምምድ እያደረጉ እንደሚገኙም ተጠቅሷል፡፡

በሌላ በኩል በፈተና ወቅት የኔትዎርክ እና የኤሌክትሪክ መቆራረጥ እንዳያጋጥም ከወዲሁ ዝግጅት መደረጉም ተነግሯል፡፡

ፈተናውን በወረቀት የሚወስዱ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ በዩኒቨርሲቲዎች ይፈተናሉ የተባለ ሲሆን፡በበይነ መረብ የሚወስዱት ደግሞ ዩኒቨርስቲዎችን ጨምሮ በመንግስትና የግል ት/ቤቶች፡በጤና እንዲሁም በመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች ፡በቴክኒክናሙያ ተቋማት እንደሚወስዱ ተነግሯል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe