ለአሰልጣኝ አስራት ሃይሌ የቀብር ስነ ስርአት ተፈጸመ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ በተጫዋችነትና አሰልጣኝነት ለረጅም ዓመታት ያገለገለው አስራት ሃይሌ (ጎራዴው) ከትናንት በስቲያ   ጥቅምት 15፣ 2017 ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወቃል፡፡

በዛሬው እለትም ወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት በአዲስ አበባ ስታዲየም የሽኝት መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

አሰልጣኝ አስራት ሃይሌ ውጣ ውረድን አልፎ በርካታ ድልን በተጫዋችነትና በአሰልጣኝነት የተቀዳጀ ጠንካራ የስፖርት ሰው የነበረ ሲሆን÷ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ጨምሮ የተለያዩ ክለቦችን በተጫዋችነትና በአሰልጣኝነት በማገልገል በርካታ ዋንጫ አንስቷል።

አሰልጣኝ አስራት ሃይሌ ውጣ ውረድን አልፎ በርካታ ድልን በተጫዋችነትና በአሰልጣኝነት የተቀዳጀ ጠንካራ የስፖርት ሰው የነበረ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ጨምሮ የተለያዩ ክለቦችን በተጫዋችነትና በአሰልጣኝነት በማገልገል በርካታ ዋንጫ አንስቷል።

አሰልጣኝ አስራት የስምንት ልጆች አባት ነበር።

ለመስከረም ኮከብ፣ ዳርማር፣ ድሬደዋ ጥጥ ማህበር፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ትግል ፍሬና ለሌሎች ክለቦች በተከላካይ ቦታ ተጫውቷል
 ሀገር ወካይ
 በ10ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በአዲስ አበባ እንዲሁም በ11ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያዎች ላይ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በተጫዋችነት አገልግሏል
 ውጤታማ አሰልጣኝ
 ስራውን በውጤት አድምቆ፥ ስኬቱን በዋንጫና በሜዳሊያዎች አጅቧል፤ ከአንዴም ሁለቴ ኮከብ አሰልጣኝ ተብሎ ተሸልሟል፤ ስሙን በደማቁ ፅፎ 38 ዋንጫዎችን ወስዷል
 ታላላቅ ክለቦችን የመራ ሙያተኛ
 ህንፃ ኮንስትራክሽን፣ ሜታ ቢራ፣ እርሻ ሰብል፣ ፊናንስ ፖሊስ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ አየር መንገድ፣ ባንክ፣ መድን፣ መከላከያ፣ መብራት ሀይል፣ ደደቢት ክለቦችን አሰልጥኗል
 የፈረሰኞቹ አንዱ ምልክት
 በተለይ በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በተጫዋችነትና አሰልጣኝነት ስሙን ተክሏል፤ በክፉ ቀን አለኝታነቱን አሳይቷል፤ በተጫዋችና በአሰልጣኝነት ክለቡን አስከብሯል
 አመራርና አርአያ
 የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንን በፕሬዝዳንትነት መርቷል፤ በቴክኒክ ዳይሬክተርነት ሰርቷል፥ ልምድና ሙያውን ያለ ስስት አጋርቷል፤ በርካታ ተተኪዎችን ፈጥሯል፤ በመገናኛ ብዙሀን በጨዋታ ትንታኔ ሙያዊ እውቀቱን አካፍሏል
 አባትና አያት
 ህዳር 15/1970 ከወይዘሮ በየነች ሰለሞን ጋር በመሰረተውና 46 አመታትን በተሻገረው የትዳር ህይወቱ የሁለት ወንድና የአምስት ሴት በአጠቃላይ የሰባት ልጆች አባት ሆኗል፤የልጅ ልጆችንም አይቷል
 ትናንት ግን…
ትናንት ጥቅምት 15/2017 የትዳር ዘመኑ 47ኛ አመት ሊሞላው ልክ አንድ ወር ሲቀረው ግን በእግርኳሳችን ታሪክ ስሙ ጎልቶ የሚነሳው አስራት ሀይሌ(ጎራዴው) ህይወቱ አልፏል፤ ስለ አገልግሎትህ ሁሉ እናመሰግናለን፤ ለቤተሰብም መፅናናትን ይስጥልን! በተለይ ደግሞ በህመሙ ወቅት ከጎኑ ሆነው ለደገፉት የክፉ ቀን ደራሽ ወገኖቹ በሙሉ ምስጋና ይገባቸዋል! እናም አስራት ሀይሌ በእግርኳሳችን ላይ ቀጣዩን ትርጉም ጨምሮልን አልፏል፦
የኢትዮጵያ እግርኳስ መዝገበ ቃላት… ቃል፦ አስራት ጎራዴው
 አቻ ትርጉም፦ ሀይለኛ፣ ደፋር፣ ቀጥተኛ፣ አልሸነፍ ባይ፣ እጅ የማይሰጥ፣ የሰላ፣ ስኬታማ
ነፍስ ይማር
(ታምሩ ዓለሙ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe