ሉዓላዊነታችንን አሳልፈን አንስጠም ሲሉ የታይዋኑ ፕሬዝዳንት ተናገሩ

ግጭት አንቀሰቅስም፤ሉዓላዊነታችንንም አሳልፈን አንስጠም ሲሉ የታይዋኑ ፕሬዝዳንት ተናገሩ፡፡

ፕሬዝዳንት ላይ ቺንግ ቴ ለባላንጋራዋ ቻይና እንዲሁም ለፕሬዝዳንት ትራምፕ ነው ጠንከር ያለ ምላሽ የሰጡት፡፡

ባለፈው ሳምንት በ ሺ እና በትራምፕ ስብሰባ ላይ የዓለምን ትኩረት የሳበችው ታይዋን አዲስና ጠንካራ አቋሟን ይፋ አድርጋለች፡፡ የደሴቷ ፕሬዝዳንት ታይዋን ለሰላም ዝግጁ መሆኗን ነገር ግን ክብሯንና ነጻነቷን ለድርድር እንደማታቀርብ በግልጽ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ሺ ለትራምፕ በሰጡት ማብራሪያ የታይዋን ጉዳይ ለቤጂንግ ቀይ መስመር መሆኑንና በሁለቱ አገራት ግንኙነት ውስጥ እጅግ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ማሳሰባቸው ይታወቃል፡፡

ይሄው ጉዳይ በአግባቡ ካልተያዘም የወታደራዊ ግጭነት መነሻ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ነበር ያስታወቁት፡፡ ፕሬዝዳንት ትራምፕም ከቤጂንግ ጉዟቸው መልስ ታይዋንን አስጠንቅቀው ነበር፡፡ ከዚህ ባለፈ አሜሪካ ከቻይና ጋር ወደ ጦርነት መግባት እንደማትፈልግም ገልጸዋል፡፡

ነገር ግን አሜሪካ ታይዋንን በተመለከተ የምትከተለው ፖሊሲ አለመቀየሩን አንስተዋል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe