ሊረዷችሁ የሚችሉ ያልተፃፉ 22 ማህበራዊ ህጎች
ሊረዷችሁ የሚችሉ ያልተፃፉ 22 ማህበራዊ ህጎች፡
- አንድን ሰው በተከታታይ ከሁለት ጊዜ በላይ አይደውሉ። ጥሪዎን ካላነሱ፣ የሚያከናውኑት አስፈላጊ ነገር እንዳለ ያስቡ፤
- የተበደራችሁትን ገንዘብ፣ የተበደራችሁት ሰው ከማስታወሱ ወይም ከመጠየቁ በፊት መልሱ። ይህ ታማኝነትዎንና ባህሪዎን ያሳያል። ይህ በዣንጥላ፣ እስክሪብቶና የምሳ ዕቃ ላይም በተመሳሳይ መልኩ ይሠራል።
- አንድ ሰው ምሳ/እራት ሲጋብዝዎት፣ በሜኑው ላይ ያለውን ውድ ምግብ በጭራሽ አይዘዙ።
- ‘ኦህ፣ ገና አላገባህም/ሽም?’ ወይም ‘ልጆች የሉህም/ሽም’ ወይም ‘ለምን ቤት አልገዛህም/ሽም?’ ወይም ‘ለምን መኪና አትገዛም/ዢም?’ አይነት አግባብ ያልሆኑ ጥያቄዎችን አይጠይቁ። በፈጣሪያችሁ! ይህ የእናንተ ችግር አይደለም፤
- ከኋላችሁ ለሚመጣው ሰው ሁል ጊዜ በሩን ክፈቱ። ወንድም ይሁን ሴት፣ ትልቅም ይሁን ትንሽ ለውጥ የለውም። በህዝብ ፊት ሰውን በአግባቡ በመያዝ ትንሽ አትሆኑም፤
- ከጓደኛ ጋር ታክሲ ከወሰዱና እሱ/እሷ አሁን ከከፈለ/ች፣ በሚቀጥለው ጊዜ ለመክፈል ይሞክሩ፤
- የተለያዩ አስተያየቶችን አክብሩ። ለእናንተ 6 የሆነው ነገር በተቃራኒ ላለ ሰው 9 ሆኖ እንደሚታይ አስታውሱ። በተጨማሪም፣ ሁለተኛ አስተያየት ለአማራጭ ጥሩ ነው፤
- ሰዎች ሲያወሩ በጭራሽ አያቋርጧቸው። ሀሳባቸውን ገልጸው እንዲጨርሱ ፍቀዱላቸው። ‘ሁሉን ስማ፣ ሁሉን አጣራ’ እንደሚባለው፤ 9 . አንድን ሰው ብትቀልዱበትና እሱ በቀልዱ እየተደሰተበት ካልሆነ ወዲያውኑ አቁሙ፤ ዳግመኛም አታድርጉት። ይህን መቀጠል ግዴለሽ መሆንዎን ያሳያል፤ 10 . አንድ ሰው ሲረዳችሁ “አመሰግናለሁ” ይበሉ።
- በአደባባይ አመስግኑ። በግል ተቹ፤
- በአንድ ሰው የሰውነት ክብደት ላይ አስተያየት ለመስጠት የሚያበቃ ምንም ምክንያት የለም ማለት ይቻላል። ዝም ብለው፣ “በጣም ታምራለህ/ያምርብሻል” ይበሉ። ስለ ክብደት መቀነስ ማውራት ከፈለጉ፣ እነሱ ራሳቸው ያነሱታል፤
- አንድ ሰው በስልካቸው ላይ ፎቶ ሲያሳያችሁ፣ ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ አታንሸራትቱ። ቀጥሎ ምን ሊኖር እንደሚችል አታውቁም፤
- የስራ ባልደረባችሁ የዶክተር ቀጠሮ እንዳለው/ላት ከነገረዎት/ች፣ ለምን እንደሆነ አይጠይቁ፣ ዝም ብለው “ደህና እንደምትሆን/ኚ ተስፋ አደርጋለሁ” ይበሉ። የግል ህመማቸውን እንዲነግሯችሁ በሚያስገድድ አላስፈላጊ ሁኔታ ውስጥ አታስገቧቸው። እንዲያውቁ ከፈለጉ፣ ያለ የእርስዎ ጠያቂነት ያደርጉታል፤
- የጽዳት ሰራተኛውን እንደ ዋና ሥራ አስፈፃሚው (CEO) በተመሳሳይ አክብሮት ይያዙ። ከእናንተ በታች ላለ ሰው ምን ያህል ባለጌ መሆን እንደምትችሉ በማሳየት ማንንም አታስደንቁም፤ ነገር ግን በአክብሮት የምትይዟቸው ከሆነ ሰዎች ያስተውላሉ፤
- አንድ ሰው በቀጥታ እያናገረዎት ከሆነ፣ ስልክዎን ማፍጠጥ የትህትና የጎደለው ነው፤
- እስካልተጠየቁ ድረስ በጭራሽ ምክር አይስጡ፤
- ከረጅም ጊዜ በኋላ ከአንድ ሰው ጋር ሲገናኙ፣ እነሱ ስለእሱ ማውራት ካልፈለጉ በስተቀር፣ ስለ እድሜያቸውና ደሞዛቸው አይጠይቋቸው፤
- ነገሩ በቀጥታ የማይመለከታችሁ ከሆነ በራሳችሁ ጉዳይ ላይ አተኩሩ – ዝም ብላችሁ ጣልቃ አትግቡ፤
- መንገድ ላይ ከየትኛውም ሰው ጋር እያወሩ ከሆነ የፀሀይ መነፅርዎን ያውልቁ። ይህ የአክብሮት ምልክት ነው። ከዚህም በላይ፣ የአይን ለአይን ግንኙነት እንደ ንግግራችሁ ሁሉ አስፈላጊ ነው፤ 21 . በድሆች መካከል ስለ ሀብታችሁ በጭራሽ አታውሩ። በተመሳሳይ፣ ልጅ በሌላቸው ሰዎች መካከል ስለ ልጆቻችሁ አታውሩ። 22 . ጥሩ መልዕክት ካነበቡ በኋላ “ስለመልዕክቱ አመሰግናለሁ” ለማለት ይሞክሩ። ማድነቅ/ማመስገን የሌላችሁን ነገር ለማግኘት በጣም ቀላሉ መንገድ ነው። እወዳችኋለሁ ! ተዋነይ – Tewanay