የገቢዎች ሚኒስቴር ኦዲት አድርጌ ደርሼበታለሁ ይከፈለኝ ያለው የታክስ እዳው 31 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ተሰምቷል፡፡
ከዩዝሆልዲንግ ታክስ እና ከቫት ቅጣት ደግሞ 473 ሚሊዮን ብር እንዳለው መግለጹ ታውቋል፡፡ ፐርፐዝ ብላክ ሜክሲኮ ላይ ሊሰራ ላስበው ባለ 115 ፎቅ መኖሪያ ህንጻ ከ 1ሺ 700 ሰዎች 1.5 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡ ይታወቃል፡፡
1.5 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ የከፈሉና አሁን ብራቸው እንዲመለስላቸው የሚጠብቁ ሰዎች ገቢዎች ሚኒስቴር አለኝ ያለውን ገንዘብ ከወሰደ በኋላ እንዲሁም ድርጅቱ ከሌሎች ተቋማት የወሰደው ገንዘብ ካለም እሱ ከተመለሰ በኋላ ነው ገንዘባቸውን ማግኘት የሚችሉት ማለት ነው፡፡
ፐርፐዝ ብላክ በዚህ ስዓት ሼር እንጂ ቤት አልሸጥኩም ለሼር ደግሞ ቫት አይከፈልም የሚል ክርክር ውስጥ መግባቱ ተሰምቷል፡፡
የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ መስራች የሆኑት ዶ/ረ ፍስሃ እሸቱ ችግሩ ከተፈጠረ በሃላ ለደህንነቴ ያሰጋኛል በማለት ለሁለተኛ ጊዜ ከሀገር ኮብልለው ወደ አሜሪካ መሰደዳቸው ይታወሳል፡፡

