መንግስት የማያውቃቸው ከ297 በላይ ኬላዎች በክልሎች እንዳሉ ተነገረ

መንግስት እነዚሁን ኬላዎች እንዲነሱ በተደጋጋሚ ውሳኔ የሰጠ ቢሆንም፤እስካሁን በክልሎች ብቻ የሚተዳደሩ 297 ኬላዎች መኖራቸው ነው ይፋ የሆነው፡፡

ኬላዎቹ እንዲነሱ ውሳኔ የተሰጠ ቢሆንም፤ክልሎች በየአካባቢው ኬላዎችን እወጠሩ የንግድ ስርዓረቱን እያወኩት ነው ተብሏል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር የ9ወራት የስራ አፈጻጸሙን ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባቀረበበት ወቅት ነው ይህን የገለጸው፡፡

በም/ቤቱ የፕላን በጀት እና ፋይናስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በክልሎች እንዲነሱ የተወሰኑ ኬላዎች ባለመነሳታቸው በገቢና በወጪ ንግዶች ላይ እንዲሁም በሸቀጦች ነጻ ዝውውር ላይ ጫና እያሳደሩ እንደሆነ ገልጻል፡፡

እነዚሁ መንግስት የማያውቃቸው ናቸው የተባሉት ከ297 በላይ የሚሆት ኬላዎች የሚገኙት ብዙም የጸጥታ ችግር በሌለባቸው አካባቢዎች እንደሆነም ታውቋል፡፡

ህገ ወጥ ኬላዎችን ለማፍረስ ስራዎች እተሰሩ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን፤አንዳንድ የጸጥታ አካላት በዚህ ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሳታፊ በመሆናቸው ችግሩ እንዳይፈታ አድርጎታልም ተብሏል፡፡/

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe