መንግስት የነዳጅ ሽያጭ ላይ 15 በመቶ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስከፈል ሊጀምር ነው

መንግስት ከነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች 15 በመቶ ቫት ሊያስከፍል ነው ተባለ። በዚህም ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ መታቀዱ ተሰምቷል።

ከመጭው ሐምሌ ወር ጀምሮ የነዳጅ ግብይትን በአለም አቀፉ ዋጋ መሰረት ይሆናል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

ላለፉት ወራት ቀስ በቀስ የነዳጅ ድጎማን እያነሳ ያለው መንግስት ሙሉ በሙሉ ድጎማውን ከማቆም ባሻገር ተጨማሪ እሴት ታክስ ሊያስከፍልበት ማቀዱ ተሰምቷል፡፡

የፌዴራል መንግስት የ2018 ረቂቅ በጀት እንደሚያሳየው ከነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች 15 በመቶ ቫት በማስከፈል ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ ማቀዱን ያሳያል፡፡

የፌዴራል መንግስት የ2018 የገቢ በጀት በሚል ለፓርላማው የቀረበው ረቂቅ በጀት ከስኳርም 1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር እና ከጨው 337 ሚሊየን ብር ተጨማሪ እሴት ታክስ ለመሰብሰብ መታቀዱን ያሳያል፡፡

ከዚህ ቀደም እንደ ዘይት እና ስኳር ያሉ ምርቶች በመንግስት የሚደጎሙና ዋጋቸውም ተመጣጣኝ እንዲሆን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የነበሩ መሆናቸው አይዘነጋም፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe