የቴክኖ ካሞን 30 ፕሮ ስልክ የፎቶግራፍ ጉዞ እና የካሜራ ብቃት ለማሳት ኤግዚቢሽን እየተካሄደ ነው
ቴክኖ ካሞን 30 ፕሮ ስልክ እና ቦርድ ሴል ፎን የፎቶግራፊ ቡድን የቴክኖ የስልክን የፎቶግራፍ እና የካሜራ ብቃትን ማሳየት አላማው ያደረገ የፎቶ አውደ ርዕይ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ለፎቶ በተመቹ አምስት መዳራሻዎች ማለትም በሀዋሳ፣ ወንዶ ገነት፣ አርባ ምንጭ፣ ኮንሶ፣ ዶርዜ መንደሮች በመጓዝ በቴክኖ ካሞን 30 ስልኮች የተለያዩ መልከዓ ምድራዊ ገፅታዎችን ፎቶዎች አንስተዋል ።
ሙሉ በሙሉ በቴክኖ ካሞን 30 እና ካሞን 30 ፕሮ የተነሱ ፎቶዎችን በመጠቀም አውደ ርዕይ በማዘጋጀት ለህዝብ ለማሳየት ቡድኑ በአምስቱ መዳረሻዎች በርካታ ፎቶዎችን አንስቷል።

ቴክኖ ሞባይል

ፎቶዎቹ ተፈጥሮን፣ እንስሳትን፣ የሰው የእለት ተእለት ኑሮን፣ መንገድን እና ባህልን የመሳሰሉ ገፅታዎች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተጠቅሷል።
በቤስት ዌስተርን ፕላስ ሆቴል የተዘጋጀው የፎቶግራፍ አውደ ርዕዩ ከሐምሌ 19 እስከ 21 እንደሚቆይ በመክፈቻው ስነ ስርዓት ላይ ተገልጿል።
በዝግጅቱ ላይ የቴክኖ አመራሮች እና ሰራተኞች፣ የቦርድ ሴል ፎን አባሎች እና የቡድኑ ተከታዮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው አንግዶች፣ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች እና የፎቶ አድናቂዎች የተገኙ ሲሆን የቡድኑን የጉዞ ቆይታ የሚያሳይ ቪዲዮም በመክፈቻ ፕሮግራሙ ለዕይታ መቅረቡ ድርጅቱ ለቁም ነገር ሚዲያ ከላከው መረጃ ለማወቅ ተችላል፡፡

