ከቀናት በፊት ኢትዮጽያን ወክላ በዓለም አቀፉ የቁንጅና ውድድር መድረክ ላይ በመሳተፍ አሸናፊ የሆነችው ሀሴት ደረጀ የ67 ሚሊዮን ብር ሽልማት ታገኛለች ተባለ፡፡
በህንድ በተደረገው ዓለም አቀፉ የቁንጅና ውድድር ላይ ሁለተኛ የወጣችው ኢትዮጽያዊቷ ሀሴት ደረጀ የ67 ሚሊዮን ብር ሽልማት እንደሚጠብቃት ተሰምቷል፡፡
ዘንድሮ ለ72ኛ ጊዜ በህንድ የተከናወነው ሚስ ወርልድ የቁንጅና ውድድር ሀሴት ደረጃ ታይላንዳዊቷን ተከትላ በ2ኛ ደረጃ አጠናቃለች፡፡
በዚህ ውድድር ከ1-3 የወጡት ተወዳዳሪዎች ይሸለማሉ፡፡ አንደኛ የወጣችው ታይላንዳዊቷ ከአንድ ሚሊዮን የዶላር ሽልማት በተጨማሪ በአልማዝ ፈርጦች ያጌጠ ዘውድ ትሸለማለች፡፡ ከዚህ ሽልማት በተጨማሪም ከተለያዩ አለም ዓቀፍ የፋሽን ተቋማት ጋር የማስታወቂያና የብራንድ አምባሳደርነት ስምምነት ታደርጋለችም ተብሏል፡፡
በዚህ ውድድር ሁለተኛ በመሆን ያጠናቀቅቸው ኢትዮጽዊቷ ሀሴት ደረጀ ደግሞ የአምስት መቶ ሺ ዶላር ወይም የ67 ሚሊዮን ብር ሽልማት ታገኛለች መባሉ ተሰምቷል፡፡
ከገንዘብ ሽልማቱ ባሻገር ደግሞ ዓለም አቀፍ የሜካፕና የፋሽን ተቋማት ማስታወቂያዎችን ያሰሯታል፡፡ እንዲሁም ሀሴት ባገኘቸው የቪአይፒ የጉዞ ጥቅል ወደ ተለያዩ የዓለም ሀገራት ነጻ የአየር በረራዎችን ማድረግ ትችላለች፡፡ በመዳረሻዎቿ ሀገራት ባሉ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴሎች ላይም የነጻ አገልግሎት ታገኛለች መባሉም ታውቋል፡፡ በዚህ ውድድር ሦስተኛ የወጣችው ፖላንዳዊት የ250ሺ ዶላር ሽልማት እንደምታገኝ ተነግሯል፡፡

