ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከ460 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ በማድረግ አዲስ አውሮፕላን ወደ ሀገር ውስጥ አስገብቷል ተባለ፡፡
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ 3 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር የሚገመት አዲስ ዘመናዊ አውሮፕላን በዛሬው እለት በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መረከቡን ገልጻል፡፡
ሴስና ካራቫን የሚል መጠሪያ ያላት ይች አውሮፕላን 14 መንገደኞችን የመያዝ አቅም ያላት ሲሆን፤ምቹ ባልሆኑ የአውሮፕላን ማረፊያዎች ጭምር ማረፍ የምትችል ናት ተብሏል፡፡
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እህት ኩባንያ የሆነው ትራንስ ኔሽንስ ኤር ዌይስ ስራ አስኪያጅ አቶ አሚር አብድልውሃብ እንደገለጹት አውሮፕላኗ በማዕድንና በእርሻ ዘርፍ የሚደረጉ ስራዎችን ለማቀላጠፍ እንዲሁም ለጎብኝዎችና ለአገልግሎት ፈላጊዎች የቻርተር አገልግሎት ለመስጠት ትውላለች፡፡
አውሮፕላኗ ከአሜሪካው ቴክስትሮን አቪሽን ኩባንያ ነው የተገዛችው፡፡ ትራንስ ኔሽን ኤር ዌይስ በአገር ውስጥ እና በአፍሪካ አህጉር የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እንደሚውል ተገልጻል፡፡//

