ሜሲ «ከእንግዲህ ከአርጀንቲና ጋር ወደዚህ መምጣት ህመም ይሆንብኛል” አለ

የእግር ኳስ ዘመን አንዱ አይነተኛ የታሪክ ምዕራፍ በእንባ ተዘጋ!
«ከእንግዲህ ከአርጀንቲና ጋር ወደዚህ መምጣት ህመም ይሆንብኛል”
የአርጀንቲናው የእግር ኳስ ንጉሥ Lionel Messi ከጨዋታው በኋላ ለአድናቂዎቹ በእጅጉ ስሜታዊ የሆነ የስንብት መልዕክት አስተላልፋል።
ሜሲ ለዓመታት በዓለም ዙሪያ የአርጀንቲናን ብሔራዊ ቡድን ሲደግፉ ለነበሩት ደጋፊዎች ምስጋናውን ገልጾ፣ የአርጀንቲና ደጋፊዎች በማንኛውም ሀገር ቢጫወቱም በቤታቸው እንደሚጫወቱ እንዲሰማቸው እንዳደረጉ ተናግሯል።
«አስቸጋሪ ጊዜዎች ይመጣሉ፤ በዚያን ጊዜ ቡድናችሁን የበለጠ መደገፍ አለባችሁ። አንድ ሆናችሁ ጠንካራ ሁኑ፤ ሌሎች ብሔራዊ ቡድኑ እንዲወድቅ የሚፈልጉ ሰዎች ደስታ እንዳያገኙ አንፈቅድም» ሲልም ጥሪ አቅርቧል።
«ከእንግዲህ ከአርጀንቲና ጋር ወደዚህ መምጣት ህመም ይሆንብኛል። በሕይወቴ ሙሉ እዚህ መጫወት እፈልግ ነበር። አርጀንቲናን መወከል ከሁሉም በላይ ውብ ነገር ነው» ብሏል።
የ2022ቱን የዓለም ዋንጫ ድል በማስታወስም፣ የራሱንና የአንድ ሙሉ ሀገርን ሕልም መፈጸማቸውን ገልጿል።
«የዓለም ዋንጫን ካሸነፍን በኋላ የመጀመሪያውን ጨዋታ እዚህ ስጫወት በሕይወቴ ከነበሩኝ ደስተኛ ቀናት አንዱ ነበር። ዛሬ ግን የምሰናበትበት ስለሆነ ምናልባት ከሁሉም አሳዛኝ ቀን ነው» ሲል በስሜት ተናግሯል።
ከዚያም ለደጋፊዎቹ፦ «በጣም እናፍቃችኋለሁ። ግን ሁሌም ከጎናችሁ እሆናለሁ። ይህን ሜዳ መልቀቅ አልፈልግም… እወዳችኋለሁ» በማለት ልብ የሚነካ ስንብት አድርጓል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe