ሞዛምቢክ ለጎረቤቷ ማላዊ ወደብ በሊዝ ለመስጠት ተስማማች

ሞዛምቢክ የባህር በር ለሌላት ጎረቤቷ ማላዊ ወደብ በሊዝ ለመስጠት ተስማማች
ሞዛምቢክ የባህር በር ለሌላት ጎረቤቷ ማላዊ የወደብ ተርሚናል በሊዝ ለመስጠት መስማማቷ ተገልጿል።
የሁለቱ አገራት ስምምነት በአገራቱ መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ ይበልጥ ለማሳደግ ያለመ ነው ተብሏል።
የሞዛምቢኩ ፕሬዝዳንት ፊሊፔ ናዩሲ እና የማላዊው አቻቸው ላዛሩስ ቻክዌራ ባሳለፍናው ሳምንት የመተማመኛ መነሻ ስምምነቱን ተፈራርማዋል።
በስምምነቱ መሠረት ለማላዊ ይሰጣል የተባለው የናካላ ወደብ በማላዊ፣ ዛምቢያ እና ሞዛምቢክ በጋራ እየተገነባ ያለው የናካላ ልማት ኮሪደር አካል ነው ተብሏል።
ይህ 722 ማይል የመንገድ አውታር ያለው የልማት ኮሪደር ግቡ ወደብ የሌላቸው ማላዊ እና ዛምቢያ ክልላዊ ትስስር እንዲፈጥሩና የባህር መዳረሻ እንዲያገኙ ማመቻቸት ስለመሆኑም የ “ዘማሪታይም ኤክስኪዩቲቭ” ዘገባ ያሳያል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe