የሩሲያ ፓርላማ አባል እና የቴሌቭዥን ፕሮፓጋንዳ ባለሙያው ሩሲያ የብሪታንያ ማህበረሰብን ለማፍረስ ሶስት ሚሳኤሎች ብቻ ይበቁናል ሲሉ ተናግረዋል።
የኘሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቅርብ ሰው እና ፓርላማው አባል ዩቬጅኒ ፖፖቭ አሜሪካ ጀርመን ውስጥ ሞስኮ መድረስ የሚችሉትን ረጅም ርቀት ተምዘግዛጊዎቹን SM-6 ከአየር ወደ አየር እና ቶማሃውክ ክሩዝ ሚሳኤሎች እንዲሁም ሃይፐርሶኒክ የጦር መሳሪያዎችን ለመትከል ማቀዷ ለእኛ ጥሩ የማንቂያ ደወል ነው ሲሉ አሜሪካና ጀርመን በዚህ ውሳኔያቸው የሚጸጸቱበትን እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀታቸውን አሳውቀዋል።
መላው ሩሲያዊያንን ጨምሮ በቀጥታ የሰሜን ኮሪያ ህዝብ በሩሲያ ሳታላይት አማካኝነት በቀጥታ በተከታተለው የቴሌቭዥን ፕሮግራም ላይ ነው የፑቲን ቀኝ እጅ የሚባሉት የፓርላማ አባል የእንግሊዝን ዋና ከተማ ለማጥፋት 3 ሚሳኤል ብቻ ይበቃናል ሲሉ የተደመጡት።
ፖፖቭ የሩሲያ መንግስት በሚቆጣጠረው የሩሲያ ብሄራዊ ቲሌቭዥን ጣቢያ ላይ በእንግሊዝ እና በስኮትላንድ ውስጥ ሰባት የተለዩ ኢላማዎችን አንድ በአንድ በዝርዝር አስቀምጠዋል።
በዚህም መሰረት የእንግሊዝ ቁልፍ የሚባሉት ከተሞች ለንደን፣ ማንችስተር፣ በርኒግሃም የተባሉ ከተሞችን ጨምሮ ሌሎችም የእንግሊዝ የጦር ሃይል፣ የሃይል አቅርቦት፣ የኒውክለር ጣቢያና ሌሎች ወሳኝ ቦታዎች ኢላማ ውስጥ መግባታቸውን አመላክተዋል። ዘገባው ከእንግሊዙ ጋዜጣ ዘ-ሰን የተወሰደ ነው።

