ሩሲያ በኢራን ላይ የመንግስታቱ ድርጅት ማዕቀብ እንዲጣልባት የሚደረገውን እንቅስቃሴ ተቃወመች

ሩሲያ ዛሬ አርብ በእንግሊዝ፡በጀርመንና በፈረንሳይ የተጀመረውን በቴህራን የኒውክሌር ፕሮግራም ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የሚያደርግ እንቅስቃሴን ተቃውማለች፡፡ ኢ3 እየተባሉ የሚጠሩት ሦስቱ የአውሮፓ አገራት ቴህራን በ2015 የገባችበትን ስምምነት ጥሳለች በሚል ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥ በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡ ሞስኮ ይህንን የአገራቱን ጥሪ አውግዛ ዓለማቀፉ ማህበረሰብም ጥሪውን እንዲያወግዘው ጠይቃለች፡፡

የ2015ቱ ስምምነት እንዲጣስም መሠረት የሆኑት አሜሪካ እና አውሮፓዊያን እንጂ ኢራን አይደለችም ብላለች፡፡ ሩሲያ ከኢራን ጋር የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት በዚህ ዓመት የተፈራረመች ሲሆን፤በሰኔው ጦርነት ወቅት እስራኤልና አሜሪካ በኢራን የኒውክሌር ጣቢያዎች ጥቃት መፈጸማቸውንም ማውገዟ ይታወሳል፡፡

ሞስኮ በቴህራን ላይ ዳግም ማዕቀብ መጣል ማለት በድርድር ለማምጣት የታሰበውን መፍትሔ ከጥቅም ውጪ የሚያደርገው ነው ብላ፤ሊያባብስ የሚችለውን የውጥረት መነሻ መከላከል እንደሚገባ አስታውቃለች፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe