ሰሜን ኮሪያ በርካታ የአጭር ርቅት ተወንጫፊ ባላስቲክ ሚሳኤሎችን አስወንጭፋለች ተባለ፡፡
ሚሳኤሎቹ የተተኮሱት በሰሜን ፒዮንጋን ግዛት ከሚገኘው የቾንግጁ ከተማ አካባቢ ነው፡፡
ሰሜን ኮሪያ ትላንት ነው በርካታ ቁጥር ያላቸውን የባላስቲክ ሚሳኤሎች ወደ ቢጫ ባህር መተኮሷን የደቡብ ኮሪያ ጦር ሃይሎች መግለጻቸውን ጠቅሶ ዮንሃብ የዜና ወኪል መዘገቡን ታስ ጽፏል፡፡
እንደ ደቡብ ኮሪ ወታደራዊ መግለጫ ከሆነ የነዚህ ሚሳኤሎች የመምታት አቅም ከ300 ኪሎ ሜትር አይበልጥም፡፡
የደቡብ ኮሪያ ጦር ባለፈው ሚያዚያ 11 በተመሳሳይ ሰሜን ኮሪያ ወደ ጃፓን ባህር በርካታ አጫጭር ርቀት ተወንጫፊ ባላስቲክ ሚሳኤሎችን መተኳሷን ይፋ አድርጎ ነበር፡፡//

