ሱዳን ለሞሮኮው የአፍሪካ ዋንጫ አለፈች

የሱዳን ብሔራዊ ቡድን ከአንጎላ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን የማጣሪያ ጨዋታ በአቻ ውጤት ማጠናቀቁን ተከትሎ ለአፍሪካ ዋንጫው ማለፉን አረጋግጧል።

በምድቡ የምትገኘው ጋና  ከኒጀር ጋር ያደረገችውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች።

ጋና በማጣሪያው ያደረገችውን ጨዋታ ማሸነፍ አልቻለችም በሶስቱ ስትሸነፍ በሶስቱ አቻ ተለያይታ የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ በመያዝ አጠናቃለች።

ናይጄሪያ በበኩሏ ከሩዋንዳ ጋር ያደረገችውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች።

ከምድቡ ናይጄሪያን በመከተል ቤኒን ለአፍሪካ ዋንጫው አልፋለች።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe