ሳውዲ ዓረቢያ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመሯን ዘጋች

የሁቲ ኃይሎች የቀይ ባህር ይዞታቸውን አጠናክረው ቀጠሉ፤ ሳውዲ ዓረቢያ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመሯን ዘጋች
የባቤል መንደብን የተቆጣጠሩት የየመን ሁቲዎች፤ በቀይ ባህር ላይ ያላቸውን ቀጥጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ያጠናከሩ ሲሆን፣ ሳውዲ ዓረቢያ ሆርሙዝን ሳትጠቀም ነዳጇን ወደ ወጭ የምትልክበት፤  ማለትም በዓለም ላይ ትልቁ ነዳጅን ወደ ወጭ የሚያስተላልፈው መስመር ጥቃት በማስተናገዱ ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ ማድረጓ ተገለጸ።

ከዚህ ቀደም፤ የባቤል መንደብን እንደሚዘጋ ሲዝት መቆየቱ የሚታወስ ቢሆንም አሁን ላይ ለመቆጣጠር ያበቃው ግን በሪያድ ከሚደገፈው የየመን መንግስት ጋር እንዲሁም ከራሷ ጋር ጦርነት በመጀመሩ ነው።

ሁቲ፤ በኢራን ከምትደግፋቸው ኃይሎች መካከል አንዱ መሆኑ የሚነገር ሲሆን፣ የየመን መንግስት ደግሞ በሪያድ እና አጋሮቹ ይደገፋል።

የነዳጅ መስመሩ ጥቃት ላይ የኢራቅ መንግስት እጅ እንዳለበትም ተሰምቷል።

ሳውዲ፤ ይህን ተከትሎ የአሜሪካን ድጋፍ መጠየቋ የተሰማ ሲሆን፣ የዚህ መስመር መዘጋት የዓለምን የነዳጅ  ዋጋ ከማወኩ ባሻገር የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን እያሰፋ አምጥቶ ግብጽ ወደ ጦርነቱ እንድትገባ ሊያደረጋት ይችላል የሚል ስጋትን አጭሯል።

ሳውዲ ዓረቢያ፤ በድሮን ጥቃት ምክንያት በሀገሪቱ አቋራጭ የሚዘረጋውን ዋና የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር በቅድመ-ጥንቃቄ ምክንያት በጊዜያዊነት መዝጋቷን ያስታወቀው  የሀገሪቱ የኃይል ሚኒስቴር ነው።

ይህ ውሳኔ የተሰማው፤ በየመን የሚንቀሳቀሱት እና በኢራን የሚደገፉት የሁቲ አማፅያን በባቤል መንደብ  እና በቀይ ባህር፤ የመተላለፊያ መስመር አቅራቢያ የሚገኙ ስልታዊ ቦታዎችን መቆጣጠራቸውን በተናገሩበት ወቅት ነው።

በሪያድ እና በመዲና በሚገኙ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ጣቢያዎች ላይ በድሮን በተፈጸመ ጥቃት የመሠረተ ልማት ጉዳት የደረሰ ሲሆን ሰዎችም እንደቆሰሉ ተነግሯል።

የሳውዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  እንደገለፀው ከሆነ፤ ጥቃቱ የተፈጸመው ከኢራቅ ግዛት በተነሱ ድሮኖች መሆኑን አስታውቋል።

የኢራቅ መንግሥት በበኩሉ፤ ጉዳዩን እንደሚያጣራ ገልፆ፣ ሳውዲ ዓረቢያ አፋጣኝ ወታደራዊ ምላሽ ከመስጠት እንድትቆጠብ ጠይቋል። የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የአካባቢውን ወታደራዊ አዛዥ ከኃላፊነት እንዳነሱ ሮይተርስ ዘግቧል።

ጥቃት ተፈፀመበት የተባለው የነዳጅ መስመር፣ 1,200 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ አለው የተባለ ሲሆን በቀን ከ4 እስከ 5 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ በማስተላለፍ የሆርሙዝ መሽመጥን ሳይነኩ ነዳጅን በቀይ ባሕር አቅራቢያ ወደሚገኝ ወደብ ለማጓጓዝ የሚያገለግል ዋና መስመር እንደሆነ ተዘግቧል።

ሁቲዎች በቀናት ውስጥ እንቅስቃሴያቸውን አስፍተው በባቤል መንደብ መግቢያ ላይ የምትገኘውን፣ ስልታዊ  ቦታ እንደሆነች የሚነግርላትን ፔሪም ደሴት  እንዲሁም ሞካ  የተሰኘች የወደብ ከተማን መቆጣጠራቸው ተገልጿል።

ይህም፤ ሁቲዎች በቀይ ባሕር የንግድ እና የነዳጅ መርከቦች ማለፊያ መስመር ላይ ያላቸውን ቁጥጥር የበለጠ አጠናክሮታል።

በነዳጅ መሠረተ ልማቶች እና በባሕር መጓጓዣ መስመሮች ላይ በተደቀነው የደህንነት ስጋት ምክንያት የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ በአንድ በርሜል ከ100 ዶላር በላይ ከፍ ማለቱን ዘገባው አመላክቷል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe