የAI ሙዚቃ፤አልበምና ኮንሠርት
ቀጣዩ የኢትዮጵያ አርቲስቶች ፈተና
እየተጠናቀቀ ባለው 2018 በርካታ አርቲስቶች ለዓመታት የለፉባቸውን የሙዚቃ አልበሞች ለአድማጮች ቢያቀርቡም የመደመጥ ዕድል ያገኙትና አነጋጋሪ የሆኑት በጣም ውስን ናቸው፡፡ ለዚህ ደግሞ የተለያዩ ምክንያቶችን መጥቀስ ቢቻልም የሙዚቃው ጥራት ጉዳይ እንዲሁም የግጥምና ዜማ ውህደት ጉዳይ በሙያተኞች አለፍ ሲልም በሙዚቃ አድማጩ በኩል ጥያቄ የሚፈጥሩ ናቸው፡፡
አንድ አልበምን በተሟላ ሁኔታ ለግጥምና ዜማ፤ ለቅንብር ባለሙያዎች ከፍሎ ማሰራት አቅም እየፈተነ መምጣቱን ተከትሎ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ አርቲስቶች የሚዘፍኗቸው ዘፈኖችን ግጥምና ዜማ ራሳቸው እየፃፉ ማቀንቀን ጀምረዋል፡፡ ይህ ደግሞ ቀደም ሲል በገጣሚነትና በዜማ አውጭነት የሚታወቁ ባለሙያዎችን ከስራ ውጭ ማስወጣቱ ብቻ ሳይሆን ያለ ተሰጥኦ የሚዘፈኑ ዘፈኖች ገበያውን እያጥለቀለቁት ነው፡፡
የዲጂታል ዓለም መስፋፋቱን ተከትሎ ለሙዚቀኞችና ለአርቲስቶች ፈታኝ እየሆነ የመጣው የ AI ሙዚቃ በአንድ በኩል የሙዚቀኞችን ድካም በመቀነስ በኩል የራሱ አስተዋፆኦ ማበርከቱ ሲነገር የፈጠራ ስራንና ባለሙያዎችን ያጠፋል በሚል የሁለት ወገን ሙግት ይቀርብበታል፡፡ ያም ሆኖ ግን ዘመኑ የዲጂታል ከመሆኑ ጋር ታያይዞ ለሙዚቀኞች ብቻ ሳይሆን ሙዚቀኛ ያልሆኑ ነገር ግን ሙዚቃን የሚወዱ ሰዎች ጭምር AI ሙዚቃ በመስራት ተደማጭ ሆነዋል፡፡ እየሆኑም ነው፡፡ ወደ ዝና ማማ እየወጡ ያሉ ግለሰቦችም ቁጥራቸው እየጨመረ ነው፡፡ ከዝናው ባልተናነሰም በ AI ሙዚቃ ገቢ በማግኘት ወደ ሃብት ማማ እየቀዘፉ ያሉ ሰዎች ለሙያተኞቹ ፈተና ሆነዋል፡፡
እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት በ AI ሙዚቃ ተሰርተው በከፍተኛ ደረጃ ተቀባይነት ያገኙ ዘፈኖች የወጡበት ዓመት ነው ለማለት ይቻላል፡፡ አንዳንዶቹ የታዋቂ አርቲስቶችን ሙዚቃዎች በ AI ሙዚቃ በመስራት መልሰው በዩቱዩብ ላይ በመጫን አድማጭ ሲያገኙ ሌሎች የራሳቸውን አዲስ የ AI ሙዚቃ በመስራት ተደማጭ መሆን ችለዋል፡፡
የሌሎች ታዋቂ አርስቶችን ዘፈኖች መልሰው በ AI ሙዚቃ በማስራት ያወጡ ሰዎች የኮፒራይትና የፈጠራ መብት ጥያቄ የሚነሳባቸው ሲሆን አዳዲስ ግጥምና ዜማ አዘጋጅተው የዘፈኑ ሰዎች ግን ራሳቸውን በሙዚቃው ዓለም ውስጥ የከሰቱ የፈጠራ ባለሙያዎች ተደርገው እየተወሰዱ ነው፡፡ ከእነዚህ ባለሙያዎች መሀከል ነዋሪነቱን በካናዳ ቶሮንቶ ያደረገው ሚልኪያስ ተፈራ በ AI ለጆሮ ገብ የሆኑ በርካታ ሙዚቃዎችን በመስራት ከታዋቂ አርቲስቶች ባልተናነሰ አልፎ አልፎም በበለጠ ሁኔታ ሙዚቃዎቹ አድማጭ ሲያገኙ የቲክ ቶክ ማድመቂያም ሆነው ታይተዋል፡፡
ሚልኪያስ መደበኛ ስራው የሙዚቃ ስራ ባይሆንም ሙዚቃን የሚወድና ግጥምና ዜማ ሰርቶ የሚያንጎራጉር ሰው ነው፡፡ AI ሙዚቃ እስኪመጣ ድረስ እንደ ሚልኪያስ አይነት ሰዎች ዘፈን ዘፍነው ስሜታቸውን ለአድማጭ የማቅረብ ዕድል አልነበራቸውም፡፡ በAI ድጋፍ ግን ስሜት ቆንጣጭ ግጥምና ዜማ በማዘጋጀትና በማንጎራጎር ከ5 ሚሊዮን በላይ ነጠላ ዜማ አድማጭ በድምሩም ከ60 ሚሊዮን በላይ አድማጭ ማግኘት ችሏል፡፡ በተለይም ‹ወይ አልወጣሁ አምባሽ ሆኜ፤ መልስ አልባ ጥያቄ፤ ኑኑዬ፤ የሚሳም ቅዳሜና ይሄውልሽ ውዴ › የተሰኙት ዘፈኖች ተጠቃሾች ናቸው፡፡
በሌላ በኩል አንጋፋውና ተወዳጁ ድምፃዊ ፀሐዬ ዮሐንስ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ AI ሙዚቃ ላይ ያለውን ተቃውሞ ከገለፁ አርቲስቶች መሀከል ተጠቃሽ ነው፡፡ ፀሐዬ የሙዚቃ ስራ የስሜት ጉዳይ መሆኑን ጠቅሶ በኮምፒዩውተር ብቻ አቀናብሮ ሙዚቃ ሰራሁ ብሎ ለመድማጭ ማቅረብ ጥበቡን መናቅ ነው ባይ ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን ሙዚቃ የሚሰራው ለአድማጭ እስከ ሆነ ድርስ በ AI የተሰራን ሙዚቃ አድማጭ እስከወደደው ድረስ ምን ማድረግ ይቻላል ለሚለው የተቀባይነት ጥያቄ የ AI ሙዚቃን የሚቃወሙ ሰዎች መልስ የላቸውም፡፡
ይልቁንም ዘፈኖቻቸው ያለ ፈቃድ በ AI ተሰርተው በየዩቲዩቡ ላይ ተጭነው ገቢ የሚያመጣ ስራ ያላቸው ታዋቂ አርቲስቶች ዘፈናቸው ያለእነርሱ ፈቃደ ሌላው ሲጠቀምበት ቆመው ከማየት ይልቅ ድርድር በማድረግ ከ AI ሙዚቃ ስራቸው ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ ቢያፈላልጉ የተሻለ እንደሆነ የዘርፉ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡ የዲጂታል መብት ጥሰትን በቀላሉ ለማስከበር ከባድ በሆነበት በዚህ ወቅት አርቲስቶች ተወዳጅ ዜማዎቻው በ AI ተሰርተው ሌሎች ሲጠቀሙበት ዳር ቆመው ከመመልከትና የመታከሚያ እያጡ ሲሞቱ ከንፈር ከመምጠጥ ይልቅ ከዘመኑ ጋር መራመድና ከዘመኑ የቴክኖሎጂ በላተኛ ስራን መጠበቅ ይገባል ይላሉ፡፡ ከአልበምም አልፈው የ AI ሙዚቃ ኮንሰርት በተለያዩ ሀገሮች እየተካሄዱ ሲሆን ቀድሞ መንቃት አስፈላጊ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ እንደአብነትም በአሜሪካ “The Crossroads Tour” – Wyatt McCoy የተባለ በ2025 የተካሄደው ዲጂታል ኮንሰርት ፈጣሪዎቹ እንደሚሉት ሙሉ በሙሉ AI የተፈጠረ ነው። ዋናው አርቲስት Wyatt McCoy የተባለ ቨርቹዋል AI ካንትሪ ዘፋኝ ሲሆን ድምፅ፣ አኒሜሽን፣ የመድረክ ምስሎችና ሙዚቃ በAI ቴክኖሎጂ ተፈጥረው በብዙ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገቢ አሰስገኝቷል።
የሙያተኞቹና በ AI ሙዚቃ ሰርተው ተደማጭ ሆኑ ሰዎችን ሙግት የሚመለከቱ ወገኖች ግን AI ለሙዚቀኞችም በሩ ክፍት ስለሆነ የፈጠራ ችሎታቸውን ይዘው ቢገቡበት የበለጠ ተደማጭ ሊሆኑ ይችላሉ በማለት ይመክራሉ፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደማጭ ሙዚቃዎችን የሰሩ አርቲስቶች ሳይቀሩ በአሁኑ ጊዜ ከ AI ሙዚቃ ለመሸሽ እንዳልቻሉና አንዳንዶቹም በ AI ድጋፍ የተቀናበሩ ሙዚቃዎችን ለአድማጭ ማቅረብ መጀመራቸውን ይጠቀሳል፡፡እንደአብነትም Xania Monet – “How Was I Supposed to Know?” በSuno AI የተፈጠረ የAI ሙዚቃ ፕሮጀክት ሲሆን በBillboard የሬዲዮ የሙዚቃ ሰንጠረዥ ላይ የገባ ከመጀመሪያዎቹ AI ዘፈኖች መካከል
በ2025–2026 የተደረጉ ጥናቶችና የሙዚቀኞች አስተያየቶች እንደሚያመለክቱት በአሜሪካ የሙዚቃ አድማጮች ስለ AI ሙዚቃ ሁለት መከራከሪያ አቋሞች አላቸው፡፡ አንዳንዶች እንደ አዲስ የፈጠራ ስራ ሲደግፉት፤ ሌሎች ደግሞ የሰውን ፈጠራና የሙዚቀኞችን ሥራ እንደሚያሳንስ ፍርሃታቸውን ይገልፃሉ፡፡
1. “AI አዲስ የፈጠራ ስራ ነው” የሚሉ
ብዙ ሙዚቀኞች AIን እንደ መሣሪያ ይመለከቱታል። ለምሳሌ የ2026 ጥናት ከ1,200 የሙዚቃ ፈጣሪዎች መካከል 78% AI መሣሪያዎችን ለመጠቀም ክፍት እንደሆኑ እና 70% ቀድሞውኑ እንደተጠቀሙ ያሳያል። (mu.se)
እነዚህ ሰዎች AIን ለየዜማ ሀሳብ ማመንጨት፤የድምፅ ማሻሻል፤የህብረ ሙዚቃ መስራት፤ሙዚቃን ለማቀናበርና ፈጣን ሙከራ ለማድረግ እንደሚጠቀሙበት ይገልጻሉ። አንድ 2026 ጥናትም የሙዚቃ ፕሮዲዩሰሮች ትልቁን የሙዚቃ ማቀናበር ሥራን በፍጥነት ለማከናወን ያግዛል ብለው ያምናሉ።
2. “AI የሰውን ፈጠራ አይተካም” የሚሉ
ይህ አቋም በሙዚቃ አድማጮች ዘንድ በጣም ጠንካራ ነው። በቅርቡ በአሜሪካ በIFPI ከ26 አገሮች ለተወጣጡ ከ43,000 በላይ ሰዎችን ያካተተ ጥናት መሠረት 79% ሰዎች AI የሰው ፈጠራ በማሳደግ ለሙዚቃ ስራ አስፈላጊ ነው ብለው እንደሚያምኑ ይፋ አድርጓል። ይህም ማለት ሰዎች AI ሙዚቃን ሊወዱት ቢችሉም፣ የሰው ስሜት፣ ልምድና ፈጠራ እንዲጠፋ አይፈልጉም።
3. ትልቁ ስጋት — የሙዚቀኞች ሥራ
በ2026 የሙዚቀኞችን ሙያ በተመለከተ በተደረገ ጥናት 79% የሙዚቃ ፈጣሪዎች AI ሙዚቃ ከሰው የተፈጠራ ሙዚቃ ጋር ስለሚወዳደር ስጋት እንዳለቸው አሳይቷል። 76% ደግሞ AI በገቢያቸው/ኑሯቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያመጣ ይችላል ብለዋል።
4. ሌላ ትልቅ ጉዳይ — “AI ወይስ ሰው?”
አስገራሚ ውጤት አለ። በ AI የሚሰሩ ሙዚቃዎች በባለሙያዎች ከሚሰሩ ሙዚቃዎች በተሸለ ተደማጭ የYመሆናቸው ጉዳይ አነጋጋሪ ነው፡፡ በቅርቡ ይህንን ሁኔታ ለመተፈተን ዋሽንግተን ፖስት ላይ በወጣ ዘገባ መሠረት 19,000 ሰዎችን በስምንት አገሮች ያካተተ ጥናት ላይ 97% አድማጮች AI የተፈጠረ ሙዚቃን ከሰው የተፈጠረ ሙዚቃ መለየት አልቻሉም ተብሏል። (Deezer Newsroom)
5. ሰዎች ግልጽነት ይፈልጋሉ
የ2023 የAI ሙዚቃ ጥናት እንደሚያሳየው 73% የሙዚቃ አድማጮች AI ሥርዓት የተጠቀመባቸውን ሙዚቃዎች በግልጽ እንዲያሳይ እንደሚፈልጉ አሳይቷል። 74% ደግሞ የአርቲስትን ድምፅ ያለፈቃድ መኮረጅ እንደማይገባ ይስማማሉ።ለዚህም ነው የሙዚቃ ኢንዱስትሪው አሁን “AI-generated” እና “AI-assisted” የሚሉ መለያዎችን ለመጠቀም እየሰራ ያለው።
ያም ሆኖ AI ሙዚቃን አይገድልም፤ የሙዚቃ አሰራርን ይቀይረዋል እንጂ። ወደፊት ምናልባት፦
ሰው + AI = አዲስ የፈጠራ ኢንዱስትሪ ሊመጣ ይችላል፡፡
ምክንያቱም AI ሰውን 100% ይተካል የሚለው አባባል አሁን የተረጋገጠ አይደለም። በተለይ ስሜት፣ የግል ልምድ፣ ባህል እና የሰው ታሪክ በሙዚቃ ውስጥ አሁንም ትልቅ ዋጋ አላቸው።
AI በመጠቀም የተሰራ የሙዚቃ አልበም ለታዳሚዎች ጥሩም፣ መጥፎም ሊሆን ይችላል። ዋናው ጉዳይ AI መጠቀሙ ሳይሆን እንዴት እና ለምን እንደተጠቀሙበት ነው።
✅ ለታዳሚዎች የሚኖረው ጥቅም
- አዲስ የሙዚቃ ሀሳቦችን በፍጥነት ለመፍጠር ይረዳል።
- አርቲስቶች በቀላሉ አዳዲስ ድምፆችንና የሙዚቃ ቅጦችን ሊሞክሩ ይችላሉ።
- የሙዚቃ ምርት ወጪንና ጊዜን ሊቀንስ ይችላል።
- ታዳሚዎች ከተለያዩ የሙዚቃ ሀሳቦች ጋር ሊተዋወቁ ይችላሉ።
❌ ለታዳሚዎች ሊያመጣው የሚችለው ችግር
- ሙዚቃው የሰው ስሜትና የአርቲስቱ ግላዊ ፈጠራ እንደጎደለው ሊሰማ ይችላል።
- ብዙ AI ሙዚቃዎች በአንድ ጊዜ ከተለቀቁ የሙዚቃ ጥራት እና ልዩነት ሊቀንስ ይችላል።
- የአርቲስቶች ድምፅ ያለፈቃድ ከተቀዳ ወይም ከተመሰለ የሥነ-ምግባርና የመብት ጉዳይ ይፈጠራል።
- ታዳሚዎች AI መጠቀሙን ካላወቁ እንደተታለሉ ሊሰማቸው ይችላል።
የሙዚቃ ባለሙያዎች በዚህ ረገድ ምክር አላቸው፡፡AI እንደ ፈጠራ መጠቀም ጥሩ ነው፤ አርቲስቱን ሙሉ በሙሉ መተካት ግን ለታዳሚዎች የሚያስነሳው ጥያቄ ብዙ ነው።በተለይ ለአልበም ሲለቀቅ፣ “ይህ ሙዚቃ AI በመጠቀም ተዘጋጅቷል” ብሎ ለታዳሚዎች ግልጽ ማድረግ የአድማጮችን እምነት ለመጠበቅ ይረዳል።
በአጭሩ፦ AI ሙዚቃ ራሱ ጥሩ ወይም መጥፎ አይደለም፤ ግልጽነት፣ የአርቲስቱ ፈጠራ፣ የድምፅ ፈቃድ እና የሙዚቃ ጥራት እንዴት እንደተጠበቁ ነው ዋናው ነገር።

